«የምክክር ኮሚሽኑ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ነው» ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ
ዓርብ፣ ጥቅምት 22 2017የኢትዮጵያ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተዋቅሮ ወደ ስራ ከገባ እነሆ ሁለት ዓመታት ሊደፍን ጥቂት ወራት ይቀሩታል ። ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ ለዓመታት መግባባት ያልተደረሰባቸው እና አፋጣን መልስ የሚሹ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሃገራዊ ምክክር እንዲደረግባቸው እና መግባባት ላይ እንዲደረስ ገንቢ ሚና መጫወት ዓላማው አድርጎ ተመስርቷል።
በድምሩ አስራ አንድ ኮሚሽነሮች የተሰየሙለት ኮሚሽኑ በአንድ ዋና እና አንድ ምክትል ዋና ኮሚሽነሮች እየተመራ ይህንኑ ታላቅ ሃገራዊ ኃላፊነት ለማስፈጸም ይንቀሳቀሳል።
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በክልሎች አጀንዳ ማሰባሰብ ሊጀምር ነው
የኮሚሽኑን ህልውና ያረጋገጠው እና ታህሳስ 2014 የጸደቀው አዋጅ በወቅቱ ብዙ ያነጋገረ ጉዳይም ነበር ።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በስራ ላይ የነበረው ኮሚሽኑ በአንድ በኩል ሀገሪቱ ካለችበት ግጭት እና ጦርነቶች የተነሳ ሃገራዊ ምክክሩን አላፈጠጠነም የሚል ቅሬታ ሲቀርብበት በሌላ በኩል ደግሞ ለገዢው ፓርቲ የወገነ እና ሌሎች ባለድርሻ ሊሆኑ የሚገባቸውን ተቃዋሚ ፓርቲዎች እና ታጣቆዎችን አላካተተም በሚል የአካታችነት ጥያቄ ሲነሳበት ይሰማል።
ሃገራዊ ምክክር በአሜሪካና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር
የኢትዮጵያ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የዚህ ሳምንት የዶቼ ቬለ የአንድ ለአንድ ዝግጅታችን እንግዳ ናቸው ።
ዋና ኮሚሽነር መስፍን ወደ ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽነርት ከመምጣታቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ መዲናዋ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ሆስፒታሎች በሐኪምነት ፣ በማስተማር እና በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች አገልግለዋል። ከተለያዩ ሃገራዊ እና አለማቀፋዊ ተቋማትም ሽልማት እና የምስክር ወረቀቶችን ማሸነፍ የቻሉ ሰውም ናቸው።
ብሔራዊ ምክክር መድረኩ የማህበረሰቡን እኩል ተሳትፎ ያረጋገጠ መሆን አለበት መባሉ
ሀገር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ በገባችበት በዚህ ጊዜ ብዙዎች በተስፋ የሚጠብቁት ሃገራዊ ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን እጅግ በጣም አስቸጋሪ የሆነውን ተቋማዊ ኃላፊነት ወስደው ከባልደረቦቻቸው ጋር በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ከኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ጋር የተዘጋጀ ብሔራዊ ምክክር
የዝግጅት ክፍሉ ለኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የኮሚሽኑን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ፣ የሚቀርብበትን ትችት እና ቅሬታ እንዲሁም በርካታ ወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ቆይታ አድርጓል።
የቃለምልልሱን ሙሉውን ይዘት ማያያዣውን በመጫን ያድምጡ ።
ታምራት ዲንሳ