የምስጋና ቀን አከባበር እና ኢትዮጽያዉያን በአሜሪካ | ባህል | DW | 24.11.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የምስጋና ቀን አከባበር እና ኢትዮጽያዉያን በአሜሪካ

በጎርጎረሳዉያኑ ህዳር ወር አራተኛ ሳምንት ሃሙስ እለት በሰሜን አሜሪካ የሚከበረዉ Thanksgiving Day ማለት የምስጋና ቀን ብሄራዊ በአል ነዉ።

default


በጎርጎረሳዉያኑ ህዳር ወር አራተኛ ሳምንት ሃሙስ እለት በሰሜን አሜሪካ የሚከበረዉ Thanksgiving Day ማለት የምስጋና ቀን ብሄራዊ በአል ነዉ። ይኸዉ እለት ቤተሰብ ጓደኛ የሚገናኝበት በቤተሰብ በአልነቱም ይታወቃል። በአመት ዉስጥ ተራርቆ ያለ ቤተሰብ ጓደኛ ከአለበት የሚሰባሰብበት በተለይ በጋራ እራት የሚበላበት በአልም እንደሆነ ጽሁፎች ይጠቁማሉ። ይህ በአል ሲዳረስ በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ አዉራጎዳናዎች እና የአየር ማረፍያዎች በተጓዦች ይጨናነቃሉ። በአሉ እለት በተለይ የዳክዪ ጥብስ የድንች ስኳር እና የድፍን ባቄላ አደንጓሪ ወጥ በአሜሪካዉያኑ የምግብ ጠረቤዛ ላይ ይቀርባል።

Obama begnadigt Truthahn

ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በምስጋና ቀን ከቀረበላቸዉ ዳክዪ ጋር

ይህ ባህል የመጣዉ በጥንት ግዜ አዉሮጻዉያን ወደ አሜሪካ ፈልሰዉ ሲገቡ ሪድ ኢንድያንስ የሚሉዋቸዉ ነባር አሜሪካዉያን መራባቸዉን አይተዉ ይህንን አይነት ምግብ ስላቀረቡላቸዉ እንደነበር ታሪክ ያሳያል።በሌላ በኩል በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጽያዉያን የምስጋናንን ቀን ቡና አፍልተዉ ዳቦ ደፍተዉ ነዉ እንደባህላቸዉ እንኳን አደረስ አደረሽ የሚባባሉት። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝዉ የኢትዮጽያ ህብረተሰብ አገልግሎት የልማት ማህበር በበኩሉ ላለፉት ስምንት አመታት ይህንን በአል ያከብር የነበረዉ በዋሽንግተን እና አካባቢዉ ቤት አልባ ኢትዮጽያዉያንን በማሰባሰብ ነበር። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic