የምስራቅ ኮንጎው ግጭት | አፍሪቃ | DW | 07.08.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የምስራቅ ኮንጎው ግጭት

ዛሬ የአፍሪቃ አገሮች ሰላም አስከባሪ ቡድን መሰረት የሚይዝበትን መንገድ ለመፈለግ የአለም አቀፍ የታላላቅ ኃይቅ አዋሳኝ አገሮች አባላት ካምፓላ ላይ ተገኝተዋል።

ሀምሌ አጋማሽ ላይ ነበር አለም አቀፍ የታላላቅ ኃይቅ አዋሳኝ አገሮች ጉባኤ ፤ በእንግሊዘኛ ምህፃሩ ( ICGLR) አዲስ አበባ ውስጥ የተካሄደው። በጉባኤውም ኮንጎ እና ሩዋንዳ ሌሎች ዘጠኝ የአፍሪቃ አገሮችን ጨምሮ ገለልተኛ የሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል ለመመስረት ተስማምተዋል። ከአፍሪቃ ህብረት አልያም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ተባብሮ ለመስራት ተወስኗል፤ የዛሬው የካምፓላ ጉባኤ የመሪዎቹ አላማ ይህን ውሳኔ መሰረት ማስያዝ ነው ። ይሁንና የተለያዩ የሀገራት ፍላጎት አንድ አለመሆን ተግባራዊነቱን አዳጋች ያደርገዋል ይላሉ ፤ከማዕከላዊው አፍሪቃ የምጣኔ ሀብት መረብ- ኢሎና አውር« ለ ICGLR ከባዱ ነገር የአባላቱ ፍላጎት የተለያየ መሆኑ ነው። በዚህም የተነሳ እነሱን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ማሰባሰቡን አዳጋች ያደርገዋል። ይህንንም በዚህ ግጭት ላይ መመልከት ይቻላል። በአንድ በኩል እነዚህ አገሮች የአለም አቀፉ ለጋሽ አገሮች ጫና አለባቸው፤ በሌላ በኩል ፍላጎታቸው በርግጥ እርስ በርሱ የሚጋጭ ነው። ይህ በጣም በጣም ከባድ ነው።»

Government troops ride on a vehicle towards the frontline where they are fighting against M23 rebels outside the eastern Congolese city of Goma, July 25, 2012. Congolese rebels and government forces traded heavy weapons fire around two eastern villages on Friday, forcing thousands of civilians to flee towards the provincial capital days ahead of a regional summit due to tackle the rebellion. REUTERS/James Akena (DEMOCRATIC REPUBLIC OF CONGO - Tags: CIVIL UNREST POLITICS CONFLICT)

ግጭት በምስራቅ ኮንጎ

ሰላም አስከባሪው ኋይል አስፈላጊነቱ ለዚህ መፍትሄ ይሆን ነበር። ራሳቸውን መጋቢት 23 ወይንም M23 በማለት የሚጠሩት የአማፂያን ቡድን በቁጥጥር ስር ያስገቧት ሰሜን ኪቩ ወሳኝ ከተማ አለች፤ እንዲሁም በስልታዊ አያያዝ ወሳኟን ከተማ ጎማን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሞከሩ ነው። ይሁንና የሀገራቱ ፍላጎት የተለያየ ነው። የኮንጎ መንግስታት ሩዋንዳ ለነዚህ አማፂያን ድጋፍ እየሰጠች ነው በማለት የተባበሩት መንግስታት የተንታኞች ዘገባን ተመርኩዘው ሲወቅሱ ሩዋንዳ ይህንን ወቀጣ በማጣጣል ዘገባው አጥጋቢ አይደለም በማለት መልሳለች።

ይሁንና ሩዋንዳ እስካሁን አለም አቀፍ የታላላቅ ኃይቆች አዋሳኝ አገሮች ባደረጉት ጉባኤ አቋሟን ስታስከብር ቆይታለች። ሰላም አስከባሪው ኃይል ርምጃ መውሰድ ያለበት በ M23 ላይ ብቻ ሳይሆን፤ በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል ተጠያቂ በሆነው በFDLR ማለትም የሩዋንዳ ነፃ አውጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይላት ቡድን ላይ ጭምር ነው። የኮንጎ የማስታወቂያ ሚኒስትር ላምበርት ሜንደ ይህን አንድ ርምጃ ነው ብለውታል።

Ehemalige FDLR-Rebellen im Reintegrationslager Mutobo im Nordwesten Ruandas

የሩዋንዳ ነፃ አውጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይላት ቡድን በአዳራሽ ተሰብስበው

«የሚያሳዝነው የኛ ጎረቤቶች ሁሌም ያላቸው አመለካከት FDLR ን መዋጋት እና M23 ን መንካት እንደማይገባ ነበር። ይህ ለምን እንደዚህ እንደሆነ እራሳችንንን እንጠይቃለን። ሰዎች በFDLR ላይ ብቻ ሳይሆን በM23 ጭምርም ተገድለዋል። ስለሆነም ሁለቱንም ንቅናቄቆች ማጥፋት ይኖርብናል። በአዲስ አበባ በነበረው ጉባኤ ለውጥ ነበር ምክንያቱም ካጋሜ M23ንም እንደ ጥሩ ያልሆነ ኃይል አስምረውበታል። ይህ አንድ ርምጃ ነው። »

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ የሰላም አስከባሪው ኃይል እንዲመሰረት በተለይ በሩዋንዳ ላይ ጫና ተደርጓል። በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የምዕራብ ለጋሽ አገሮች ሩዋንዳን የገንዘብ ድጎማቸውን ከልክለዋታል። ኢሎና አውር ፤ ሌላም ችግር አንስተዋል። ይህም በርካታ ሀገራት ከኮንጎ ያልተረጋጋ ሁኔታ ያተርፋሉ፤ እንደ ምሳሌ የጠሯትም አገር ዮጋንዳ ናት፤« እንደሚመስለኝ ዮጋንዳንም ምን አይነት ፍላጎት እንዳላት መመርመር ይገባል። ለነገሩ ዮጋንዳ በጉዳዩ ላይ እንደ ሩዋንዳ በስፋት አልተሳተፈችም። በተረፈ ሌሎቹ አገሮች ራሳቸውን ጣልቃ ሳያስገቡ አልያም የበለጠ ግጭቱ እንዳይጠናከር ከነገሩ ተቆጥበው የሚቆዩ ይመስለኛል። ሁኔታው እንዲረጋጋ ይፈልጋሉ።»

በርካታ ታዛቢዎች ካለው የገንዘብ ችግር ተነስተው የአለም አቀፉ የታላላቅ ኃይቆች አዋሳኝ አገሮች ጉባኤ ውጤት ከመልካም ምኞት ያለፈ እንደማይሆን ከወዲሁ ግምታቸውን ሰንዝረዋል። የአፍሪቃ ህብረት እኢአ በ2005 ወደ ኮንጎ ሰላም አስከባሪ እንዲላክ ቢወስንም ተልኮው ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።

ፊሊፕ ሳንድነር

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 07.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15kr7
 • ቀን 07.08.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15kr7