የምስራቃዊ ኮንጎ ዉጥረትና የተመድ ዘገባ | አፍሪቃ | DW | 20.10.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የምስራቃዊ ኮንጎ ዉጥረትና የተመድ ዘገባ

የተለያዩ ሚሊሺያ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱበት ምሥራቃዊ ኮንጎ አሁንም ውጥረት ይታይበታል። ርዋንዳና ዩጋንዳ ይህንኑ ያማፂ ቡድን እንደሚያስታጥቁና እንደሚያደራጁ ሰሞኑን ሾልኮ የወጣ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ አስታወቀ።

የተለያዩ ሚሊሺያ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱበት ምሥራቃዊ ኮንጎ አሁንም ውጥረት ይታይበታል። በተለይ በዚሁ አካባቢ ከሚገኘው የሰሜን ኪቩ ግዛት ከፊሉን የያዙት ኤም 23 በመባል የሚታወቀው ቡድን ሚሊሺያዎች ሕዝቡን ማሸበራቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ ይገኛሉ።

የተመድ ወደ ሰሜናዊ ማሊን ከተቆጣጠሩዋት ሙስሊም ፅንፈኞች በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ለማስለቀቅ የሚቻልበትን ዕቅድ ተግባራዊ የማድረጉን መንገድ አመቻችቶዋል። ይህ ተልዕኮ የሚጀመር ከሆነ ዓለም አቀፉ የመንግሥታት ድርጅት በአፍሪቃ የሚያካሂደው ስምንተኛው ተልዕኮ ይሆናል ማለት ነው። እነዚህ ዕነቶቹ ተልዕኮዎች ምን ያህል ስኬታማ ናቸው? የብዙዎች ጥያቄ ነው። የርዋንዳ ላይ የሚሰማው ወቀሳና የተመድ ተልዕኮ በአፍሪቃ የተሰኙት ሁለት ጉዳዮች የዛሬው ትኩረት በአፍሪቃ የሚያተኩርባቸው ናቸው።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሽ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች