የምርጫ ጊዜ ተራዘመ | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የምርጫ ጊዜ ተራዘመ

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈዉ ደብዳቤ ግን ዘንድሮ ምርጫ ለማድረግ አስተማማኝ ፀጥታ ባለመኖሩ የምርጫዉ ጊዜ በአንድ አመት እንዲራዘም ጠይቋል።ምክር ቤቱም የቦርዱን ጥያቄ ተቀብሎ ምርጫዉ በ2011 እንዲደረግ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:19

የከተሞቹን የአስተዳደሪነት ሥልጣን  የሚረከበዉ ወገን ማንነት ግን በዉል አልታወቀም።

የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ መስተዳድሮች የምክር ቤት አባላት ምርጫ በአንድ ዓመት እንዲራዘም የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወሰነ።የሁለቱ ምክር ቤቶች እና የፌደራሉ ምክር ቤት  የማሟያ ምርጫ በቅርቡ ይደረጋል ተብሎ ነበር።ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፃፈዉ ደብዳቤ ግን ዘንድሮ ምርጫ ለማድረግ አስተማማኝ ፀጥታ ባለመኖሩ የምርጫዉ ጊዜ በአንድ አመት እንዲራዘም ጠይቋል።ምክር ቤቱም የቦርዱን ጥያቄ ተቀብሎ ምርጫዉ በ2011 እንዲደረግ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።በስልጣን ላይ ያሉት የሁለቱ ከተሞች አስተዳደር ዘመነ ሥልጣን ዘንድሮ ሥለሚያበቃ የከተሞቹን የአስተዳደሪነት ሥልጣን  የሚረከበዉ ወገን ማንነት ግን በዉል አልታወቀም።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

 

Audios and videos on the topic