የምርጫ ዝግጅትና ተቃዉሞዉ በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 12.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምርጫ ዝግጅትና ተቃዉሞዉ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል።

default

ኢትዮጵያ ዉስጥ የመፊታችን ዕሁድ እና በሳምንቱ ዕሁድ በሚደረገዉ አካባቢ ምርጫ ከሠላሳ-አንድ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፁን ለመስጠት መመዝገቡን የሐገሪቱ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ እንደገለጡት በሁለት በተከፈለዉ ምርጫ ሃያ-አራት የፖለቲካ ፓርቲዎችን የወከሉ ከስድስት ሚሊዮን በላይ እጩዎች ይወዳደራሉ። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር አቶ ይስማ ጅሩን አነጋግሯቸዋል።የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙት ሠላሳ ሰወስት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ግን በመጪዉ ዕሁድ በሚጀምረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ላለመሳተፍ ወስነዋል።ፓርቲዎቹ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ያገለሉበትን ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማስረዳታቸዉን አስታወቀዋል። የጋራ ትብብር የመሠረቱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ቅድመ-ሁኔታ ካልተሟላ በምርጫዉ እንደማይሳተፉ በተደጋጋሚ አስታዉቀዉ ነበር። የጋራዉ ትብብር መሪዎች እንዳሉት ይሕን ምክንያታቸዉን ሠሞኑን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገልፀዋል። በተመሳሳይ ዜና የሲዳማ አርነት ንቅናቄም በምርጫዉ እንደማይታፍ አስታዉቋል። የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት እንደሚሉት አባላቶቻቸዉና ደጋፊዎቻቸዉ ይታሰራሉ፥ ይሸማቀቃሉም። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic