የምርጫ ዉዝግብ እና የተቃዋሚዎች ፓርቲ ክስ | ኢትዮጵያ | DW | 14.06.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምርጫ ዉዝግብ እና የተቃዋሚዎች ፓርቲ ክስ

የአራተኛዉን ዙር ብሄራዊ ምርጫ እንዲደገም ከጠየቁ ተቃዋሚዎች መካከል መኢአድ ዛሪ ለጠቅላይ ፍርድቤት የክስ ማመልከቻ አስገብቶአል።

default

በሌላ በኩል መድረክ ለፍርድ ቤት ያቀረበዉ ተመሳሳይ ጥያቄ ዉድቅ እንዲደተደረገበት አስታዉቆአል። መድረክ የም/ቤቱ ምርጫ መጭበርበሩን በማመልከት ድምጽ-አሰጣጡ እንደገና እንዲካሄድ ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው ማመልከቻ በመረጃ ጉድለት አስባብ በቅርቡ ውድቅ መደረጉ የሚታወስ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሃይለጊዮርጊስ ከመኢአድ ዋና ፀሃፊዉን እና ከመድረክ ምክትል ፕሪዝደንቱን አነጋግሮ ዘገባ ልኮልናል።


ጌታቸዉ ተድላ ሃ/ጊዮርጊስ፣ አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ