የምርጫ ወግ በጀርመን | ባህል | DW | 26.09.2009
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

የምርጫ ወግ በጀርመን

Geh wählen! ይሰኛል በጀርመን ዋናዉ የጀርመን የምክር ቤት ምርጫ ከመቃረቡ አራት ሳምንት በፊት ጀምሮ በጀርመን የራድዮ እና የቴሌቭዥን ጣብያዎች ሲያስራጭ የነበረዉ የምርጫ ቅስቀሳ።

default

በማስታወቅያዉ ላይ በጀርመን ታዋቂ ፊልም አክተሮች ጋዜጠኞች ወይም የመድረክ ሰዎች ይገኙበታል።
በጀርመን በመካሄድ ላይ ያለዉ ምርጫ ሊጠናቀቅ የቀረዉ አንድ ሰአት ነዉ። ከምርጫዉ በኋላ የትኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከየትኞቹ ተጣምረው አዲሱን ፌዴራዊ መንግስት ይመሰርታሉ በሚል ከወራቶች በፊት ጀምሮ ትልቅ አነጋጋሪ ርእስ ሆኖ ሰንብቶአል። በተለይ ባለፈዉ እሁድ እዚህ በባቫርያ ግዛት በሙኒክ ከተማ ለ 176ኛ ግዜ በተከፈተዉ በባህላዊዉ የቢራ ድግስ ላይ ታዋቂ የአገሪቷ ፖለቲከኞች ታዋቂ የመድረክ ሰዎች ከያኒያን እና የፊልም ስራ አዋቂዎች በቢራ ድግሱ ላይ ለብሰዉት ከሚታዩበት የባህላዊ አልባሳት ለጥቆ ትልቁ ርእሳቸዉ የነበረዉ ይኸዉ በጀርመን በመካሄድ ላይ ስላለዉ የምረጡኝ የፖለቲካ ቅስቀሳ አልያም ደግሞ የትኛዉ የፖለቲካ ፓርቲ ከየትኛዉ የፖለቲካ ፓርቲ ተጣምሮ አዲሱን ፊደራላዊ የጀርመን መንግስት ይመሰርታል በሚለዉ ላይ ነበር። ሲገኛኙም ታድያ በቋንቋቸዉ Geh wählen “ለምርጫ ዉጣ“ የሚለዉን ማስታወቅያ ሳያነሱ አላለፉም። እዚህ በቦን ከተማ አጠገብ በምትገኝዉ ሜከን ሃይም ከተማ ዉስጥ ነዋሪ የሆኑት እና በቦን ከተማ በመንገድ ስራ ተቋራጭ ቢሮ ዉስጥ ሰራተኛ የሆኑት ጀርናመናዊዉ ራይን ሆልድ ሽሚት በአገራቸዉ የሚካሄደዉ የምርጫ ሂደት ፍትሃዊ ዲሞክራስያዊ፣ እናም የምርጫዉ ዉጤት ክቡር መሆኑን በኩራት ይገልጻሉ። ለዛሪዉ ምርጫ ተዘጋጅተዋል የመጀመርያዉ ጥያቅያችን ነበር
«አዎ ባይገርምሽ መርጫለሁ፣ ከአንድ ሳምንት በፊት ነዉ የመረጥኩት፣ ማለቴ ከምርጫ ጣብያ የምርጫ ቅጽ እንዲላክልኝ ተናግሪ ቅጹ በፖስታ ደረሰኝ፣ የምመርጠዉን መርጬ መልሼ ልክያለሁ። ለነገሩ በፖስታ ብቻ ሳይሆን እዝያዉ የምርጫ ጣብያ ሄዶ የምርጫዉን ቅጽ ሞልቶ መስጠትም ይቻላል። ምርጫዉ የተጀመረዉ ከአራት ሳምንት በፊት ነዉ። ዛሪ ግን የመጨረሻዉ እና ዋንኛዉ የምርጫ ቀን ነዉ»
እንደ ራይን ሆልድ ሽሚት በመጨረሻዉ እና በዋናዉ የምርጫ ቀን ማለት በዛሪዉ እለት በስራ ጉዳይ ወደ ሌላ አዉሮጻ አገር በመሄዳቸዉ ነዉ የምርጫ ቅጹን በፖስታ አሽገዉ ወደ ምርጫ ጣብያ የላኩት፣ ያም ሆነ ይህ ይያላሉ ራይን ሆልድ ሽሚድ፣ ማንኛዉ የጀርመን ዜግነት ያለዉ የጀርመን ነዋሪ፣ ነዋሪነቱ በዉጭ አገር ቢሆን በአካባቢዉ በሚገኘዉ የጀርመን የዉክልና ቢሮ ድምጹን ይሰጣል። በጀርመን አገር በምርጫዉ እለት ህዝቡ ድምጹን ከሰጠ በኻላ በምርጫዉ ዙርያ ምን የተለመደ ወግ አለ ሌላዉ ጥያቅያችን ነበር
«በመጨራሻዎቹ አመታት የምርጫ ጣብያዎች ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት ላይ እንደተዘጉ በአብዛኛዉ ማለት ይቻላል፣ ቤተሰብ ተሰባስቦ ቆሎ ብጤ እየቆረጣተመ እና ቢራ እየጠጣ የምርጫዉን ዉጤት ይጠባበቃል። አብዛኛዉን ግዜ ምርጫዉ እንደተጠናቀቀ በአንድ ሰአት ግዜ ዉስጥ በተለያዩ ግዛቶች የድምጽ ቆጠራዉ እየተደረገ በተያያዘ ያለዉ ዉጤት ይፋ መደረግ ይጀምራል። ያ ማለት በምርጫዉ የመጀመርያ ዉጤት የተደሰተ ቢራዉን በደንብ መጠጣት ይጀምራል። በመጀመርያዉ ዉጤት የተበሳጨም ለብስጭቱ ማብረጃ እንዲሁ!»

Oktoberfest in München 2009


በርግጥ በጀርመን በሚካሄደዉ የምርጫ ወቅት እንደ አዲስ አመት እንደ ገና ወይም እንደ ፋሲካ በአል በቤተሰብ ዉስጥ ተሰባስቦ ምግብ አብስሎ አብሮ ገበታ የመቅረብ ባህል ባይኖርም የሚሉት ራይን ሆልድ ሽሚት፣ በዘንድሮ አመት በሙኒክ ባየር ዉስጥ የሚካሄደዉ የቢራ ድግስ ዝግጅት ሰበብ በሙኒኩ የቢራ ድግስ ላይ ብቻ ሳይሆን ሰሞኑን ጥሩ የሰነበተዉ የአየር ሁኔታ በየተለያዩ የጀርመን ከተማዎች ዳስ ተጥሎ የቢራ ድግስ እንዲካሄድ እና በየአራት አመቱ ስለሚካሄደዉ የጀርመን የምክር ቤት ምርጫ ሰበብ ህዝቡን እንዲሰባሰብ እና እንዲወያይ አድርጎታል ባይ ናቸዉ። በሌላ በኩል ይላሉ በጀርመን ምረጥ ብሎ ግዴታ የለም፣ ነገር ግን ህዝቡ እንዲያስተዳድረኝ እፈልጋለሁ ብሎ ያለዉን ዲሞክራሲና የፍትህ ሁኔታ ተጠቅሞ ቤተሰቦቹን ይዞ ለአቅም አዳም ያልደረሱ ልጆቹንም አስከትሎ የምርጫዉን ሂደት ሊያሳይና ለአገሪ ይህ ይሻላል ያለዉን ሊመርጥ በኩራት ወደ ምርጫ ጣብያ ይወጣል።
«በጀርመን በሚካሄደዉ የምርጫ ግዜ በአብዛኛዉ ቤተሰብ በጋራ ተሰባስቦ ነዉ ወደ ምርጫዉ የሚሄደዉ፣ ልጅ እናት አባት ማለት ልጅ ለመምረጥ እድሜዉ ከደረሰ ማለት ነዉ፥ ከምርጫ መልስ ወደ አንድ አነስ ባለች ቡና ቤት ገብቶ ቡና ብስኩት ብቴ ይበላል። ስለ ምርጫዉ ሂደት ይወያያል፣ በምርጫዉ ጣብያ በርካታ ሰዉ በቤተሰብም ቢሆን ማን ማንን እንደመረጠ አይጠያየቅም አመሻሽ ላይ ደግሞ ቢራ ወይም ወይን ይዞ የምርጫዉን ዉጤት ለመስማት ቴሌቭዥን ይከታተላል»
በዋንኛዉና በመጨረሻዉ የምርጫ ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰአት የጀመረዉ የምርጫ ሂደት ልክ ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት ላይ ይጠናቀቃል። እንደ ልምዴ ይላሉ ራይን ሆልድ ሽሚት አብዛኛዉ ህዝብ ለምርጫ ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ግድም ላይ ነዉ በብዛት ሲወጣ ያየሁት። በጀርመን በሌሎችም ምዕራባዉያን አገሮች መምረጥ የዜጎች መመብት መሆኑ የተረጋገጠበት፣ የድምጽ መጭበርበርበር የማይታይበት፣ አንድ ዜጋ አደባባይ ወጥቶ መምረጡ ለዲሞክራሲ መቆሙ የሚረጋገጥበት፣ የምርጫዉም ዉጤት በክብር ተቀባይነት የሚያገኝበት፣ የምርጫ ወግ አለ።
ሌላዉ ይላሉ አንድ ፖለቲከኛ ለአገሩ ለፓርቲዉ አገልግሎ ከመድረክም ሲገለል በክብር ነዉ ይህም አንዱ የምርጫ ወጋችን ነዉ። በተለይም ይላሉ በመራሄ መንግስቱ ቢሮ የጀርመን ፊደራላዊ ሪፐብሊክ ከተቋቋመ ጀምሮ የነበረ የጀርመን ካንስለር ማለት መራሄ መንግስት ፎቶ በቢሮዉ ተጠልጥሎ ይገኛል።
«በምርጫዉ ሂደት እንደ አዉሮጻዉያን አቆጣጠር 1985 አ.ም ግድም ጀምሮ ለመራሄ መንግስትነት የቀረቡ እጩዎች ለጀርመን ህዝብ የፖለቲካ አቋማቸዉን በመግለጽ የሚከራከሩበት እና የሚነቃቀፉበት መድረክም ተጀምሮአል። ይህ በጀርመን አንዱ ትልቅ የምርጫ ወግ ሆንዋል» በመድረኩ ይላሉ «እጩዎቹ አራት ሳምንት ሲቀረዉ ነዉ ህዝብ ፊት በቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ የሚቀርቡት»

Flash-Galerie Woche 38_09


በጀርመን የምርጫ ወቅት የተለያዩ ፓርቲዎች በየረድፋቸዉ የምረጡን ቅስቀሳቸዉን ሲያካሂዱ መርሆአቸዉን በየቦታዉ ሲያሳዉቁ የጦር መሳርያ የታጠቀ ጦር ሰራዊት አልያም ማስፈራርያ ዱላ የያዘ የሌለበት መራጮች የምርጫ ካርዳቸዉን ይዘዉ ቤተሰቦቻቸዉን አስከትለዉ የነገዋን አዲስቱዋን ጀርመን ይመራል ያሉትን ለመምረጥ ዉጤቱን በምኞት በጉጉት ከመጠበቅ ባሻገር በምርጫ ወጋቸዉ የሚያስቡኡት የሚገምቱት ነገር የለም።
ለዚህም ነዉ በየትያትር ቤቱ በየስፖርት ሜዳዉ እንዲሁም ከምርጫ ዉጤት በኻላ በሚደረገዉ የዳንኪራ ምሽት በኩራት የብሄራዊ መዝሙራቸዉን ሁሉም የአገሪቷ ፓርቲዎች በጋራ የሚዘምሩት። ይህ ባህል ይህ ወግ ወደ አፍሪቃችን ገብቶ ተመሳሳይ ፍትሃዊ ዲሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት፣ የባህል ግንባታ ቢመጣ የሁላችን ምኞት ይመስለናል።

 • ቀን 26.09.2009
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/Jpiw
 • ቀን 26.09.2009
 • አዘጋጅ Azeb Tadesse
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/Jpiw