የምረጡኝ ቅስቀሳ | ኢትዮጵያ | DW | 10.05.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የምረጡኝ ቅስቀሳ

ለግንቦት 15 2002 የታቀደዉ አገራዊ ምርጫ በተቃረበበት በዚህ ወቅት የየተፎካካሪ ፓርቲዎቹ የምረጡኝ ቅስቀሳ ተጠናክሮ መቀጠሉ ነዉ የሚነገረዉ።

default

የህዝብን ድጋፍ ለመሻት የአደባባይ ስብሰባ በመንግስት የተከለከለ መሆኑ በይፋ የተገለጠ ቢሆንም፤ በትናንትናዉ ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲዮም የገዢዉ ፓርቲ ደጋፊዎች ተሰባስበዉ ድጋፋቸዉን ገልጸዋል። በአንፃሩ ከተቃዋሚዎች የስምንት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የኢትዮጵያ ፌደራሊስት አንድነት መድረክ በጎፋ ሰፈር የወጣቶች መሰብሰቢያ አዳራሽ ስብሰባ አካሂዷል። የወኪላችን የጌታቸዉ ተድላ ዘገባ ሁለቱንም ይዳስሳል

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ