የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓል በቫቲካን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 08.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓል በቫቲካን

የሮማዉ ካቶሊካዊት ቤተ- ክርስትያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን እና ፖለቲከኞች በተገኙበት በቫቲካን ታላቅ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓልን በይፍ ከፈቱ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:31
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
02:31 ደቂቃ

የምህረት ዓመት ክብረ በዓል በቫቲካን

በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ ስርዓተ-ፀሎት ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ «ፍርኃትና ሰቆቃን ወደኃላ መጣል ያስፈልገናል» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በኢጣልያ ዋና ከተማ በሮም የፀጥታ ጥበቃው ተጠናክሮ በአብዛኛዉ ቦታ የበረራ እገዳ ተደርጎ ነበር ፤ ማንኛዉም አይነት ነዳጅም ሆነ የጦር መሣርያን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎe ወደ ከተማይቱ ማዕከል እንዳይወጡ ተክልክለውም ነበር ። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በሮማ ኢጣልያ ወኪላችንን ተክለዝጊ ገብረየሱስን፤ ስለ ምኅረት ቀን ምንነትና ዝግጅቱ ጠይቄዉ ነበር

ተክለዝጊ ገብረየሱስ

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic