የሜርክል ፖለቲካዊ ሰብዕና | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 10.09.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሜርክል ፖለቲካዊ ሰብዕና

እጅግም መኳኳል ያልለመደ ገጻቸዉን፤ ኋላቀር የጸጉር ፋሽናቸዉንና አለባበሳቸዉን በማየት ብስል ፖለቲከኛ ይሆናሉ የሚል ግምት እንዳልነበረ ብዙዎች ይስማማሉ። ሆኖም ግን አንጌላ ሜርክል አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ የጀርመን መርሂተ መንግስት ለመሆን ለምርጫ ፉክክር ተዘጋጅተዋል።

አንጌላ ሜርክል ፖለቲካን እንዴት እንደሚሠሩ ለማወቅ የሚሻ ካለ ትላለች ያኔተ ዛይፈርት ከአሜሪካዉ የስለላ ተቋም NAS ጋ በተገናኘ የተነሳዉን ዉዝግብ እንዴት ዉሃ እንደደፉበት ማስተዋል ይገባዋል። በመሠረቱ ይህ የፖለቲካ ቅሌት በመራሄ መንግስቷ የአገርም የዉጭም ፖለቲካ ላይ አደጋ ያስከትል ነበር። ሜርክል ጉዳዩ በመገናኝ ብዙሃን ተነስቶ ክርክሩ በጦፈበት ወቅት ምላሽ ለመስጠት አልፈጠኑም። ከዚያም ረጋ አሉና መጀመሪያ በቃል አቀባያቸዉ አማካኝነት ጉዳዩን አነሱ፤ በመቀጠልም ከአንድ ቴሌቪዥን ጋ ባደረጉት ቃለመጠይቅ እንዲህ ባለዉ የመረጃ ልዉዉጥ ከመተባበር ወደኋላ ማለት እንደሚያዳግት ገለጹ፤

Helmut Kohl Feierlichkeiten 20 Jahre Deutsche Einheit

ሜርክል ከሄልሙት ኮኽል ጎን

«ሁለት ነገሮችን ማድረግ የሚኖርብን ይመስለኛል፤ ሀ/ የስለላ ተቋም ያስፈልገናል፤ ለ/ እነሱም በዴሞክራሲያዉ የሕግ ስርዓት ስር መሆን አለባቸዉ፤ ወይም የሥራቸዉ ባህሪ የሚፈቅድላቸዉ እስከሆነ ድረስም አሰራራቸዉን የግድ የሚገልጹበት ሁኔታ እንዲኖር ማድረግ ይኖርብናል።»

በዚህ መልኩ ችግሩን ወደጎን በማድረግ በብዙሃኑ ሃሳብ ነገሩን ቋጩት። ብዙዎች ይህን «የሜርክል ስልት» ይሉታል። ለፖለቲካ ተሰጥኦዋቸዉ የሚቸር አክብሮትና አድናቆት መሆኑ ነዉ። ሜርክል ጠንካራ ጎናቸዉን ደግመዉ ደጋግመዉ የሚያስፈትሹበት አፋጣሚ ተፈራርቋል። ከምንም በላይ በአዉሮጳ መድረክ፤ ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2008ዓ,ም አንስቶ መራሂተ መንግስቷ ዩሮን ለማዳን ባደረጉት ጥረት የቀዉስ አፈታትና አያያዛቸዉ አይን አሳርፎባቸዋል። እርግጥ ነዉ ባራመዱት የቁጠባ ርምጃ ምክንያት በሁሉም ቦታ ስለእሳቸዉ በጎ ይነገራል አይባልም። ለዩሮ ፓለቲካቸዉ ግን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተሰጣቸዉ አድናቆት ያመዝናል፤

«ምንም እንኳን በፓርቲያቸዉ ዉስጥ ይህን የሚቃወሙ ቢኖሩም በብልህነት ጀርመን ዉስጥ ዩሮ አያዋጣም ብለዉ የሚገምቱትን የሚያረጋጋ የኤኮኖሚ ተሃድሶ ለዉጥ በማድር የአዉሮጳ ወዳጆችንም ሊያረኩ ችለዋል። ያረካ በስልት የተቀመረ የኤኮኖሚ ማሻሻያ ማድረግ ተሳክቶላቸዋል።»

በማለት ያብራራል ደራሲና ጋዜጠኛ ራልፍ ቦልማን። ከጎርጎሪዮሳዊዉ 1945ዓ,ም ወዲህ በጀርመን ታሪክ እንደየጀርመኗ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ቄስ ልጅ እንደሜርክል ዝቅተኛ ግምት የተሰጠዉ ፖለቲከኛ አልነበረም።

Flash-Galerie Angela Merkel 1992 Bundesministerin für Frauen und Jugend

ሜርክል በሚኒስትርነት መአረግ

«ብዙዎች ከአስርት ዓመታት በላይ «በዚህች ልጅ» ሲቀልዱ ቆይተዋል፤ ልክ ሄልሙት ኮል እንደሚሏቸዉ ማለት ነዉ። አሁን ግን ልዩነቱን ለሚያየዉ የፖለቲካ ሰብዕናቸዉ ግልፅ ነዉ።»

የመራሂተ መንግስቷን የህይወት ታሪክ የጻፈችዉ ጋዜጠኛ ጃክሊን ቦይዘን ታስታዉሳለች። በተረጋጋዉ የመንግስት አስተዳደራቸዉ ግን ከፓርቲያቸዉ አልፎ በሌሎችም ዘንድ አክብሮትን እንዳተረፉ ትገልጻለች።

«መከራከሪያ ነጥቦችና እዉነታዎችን ያሰባስባሉ፤ ከዚያም ከዉሳኔ ላይ ይደርሳሉ፤ እንዲህ በነፃ መንፈስ እዉነታዉን ወይምየመረጃ ስብስቦችን በመንተራስ ዉሳኔ ያሳልፋሉ።»

የፓርቲያቸዉንም ርዕዮተዓለምና መርሃግሮች ለማስተሳሰር ጊዜ ወስደዉ ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ፈታ ያለ አካሄዳቸዉም ለምርጫ ቅስቀሳ የሜርክል ጠንካራ ጎን ነዉ። ተጨባጩን ሁኔታ መከተልም ከሁሉም ነገር ይበልጥባቸዋል። እናም የቆየ አቋማቸዉን ፈጥነዉ ለመከለስ አያዳግታቸዉም። በፉኩሺማ ከታየዉ የኒኩሊየር ጨረር አደጋ በኋላ የኒኩሊየር መርሃ ግብራቸዉን የማሻሻሉ ርምጃቸዉ ጉዳት አላስከተለባቸዉም። ይልቁንም የድሮዉ መራሄ መንግስት «ኮህል ልጅ» ይባሉ የነበሩት ሜርክል «እናታችን» ወደሚለዉ የቁልምጫ እርከን ከፍ ለማለት ፈጥነዉ በቁ እንጂ። ሜርክል ፓርቲዉንም መንግስቱንም በአጭር ጊዜ ነዉ በእጃቸዉ ያስገቡት። ምናልባትም የአስተዳደር ብስለት የተካኑት በቀድሞዋ ዴሞክራቲክ ጀርመን ባሳለፉዋቸዉ ጊዜዎች ዉስጥ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ አሉ። በወቅቱ አንጌላ ሜርክል የየትኛዉም ወገን ፖለቲካ ደጋፊና ተቃዋሚ አልነበሩም።

«ከሁሉም በላይ የፈለጉትንማድረግበማይቻልበትስርዓትዉስጥማደጋቸዉእንደቀረጻቸዉግልጽነዉ።»

Cloppenburg Wahlkampf CDU Merkel

የምርጫ ቅስቀሳ

ትላለች የህይወት ታሪካቸዉ ጸሐፊ ቦይዘን። ከሌሎች ጋ በጥንቃቄ እንዴት አብሮ መጓዝ እንደሚቻል አስቀድመዉ የተማሩ ይመስላል። እናም ካሏቸዉ ግሩም መለያዎች አንዱ የሆነዉን ማዳመጥን ሥራዬ ብለዉ ነዉ የተያያዙት። ወጣቶችም ሆኑ አዋቂዎች አድናቂዎቻቸዉ የእሳቸዉ ከፍተኛ የመግባባት ችሎታ ይስባቸዋል። ሰሞኑን በሚያደርጉት የምረጡኝ ዘመቻም አንዳንዴ ስለግል ህይወታቸዉ ሲናገሩ ተስተዉለዋል፤ ለምሳሌ ኬክ መጋገር እንደሚወዱ ሆኖም ባለቤታቸዉ እላዩላይ የሚያደርጓቸዉ ጌጦች ስለሚያንሱ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፤

«እኔ ትሁት ሰዉ ነኝ፣ ለምጠየቀዉ ጥያቄ ምላሽ እሰጣለሁ። ስለግል ህይወቴ በምናገርበት ጊዜ በቃ ስለፖለቲካ ማዉራቱን ተወች እባላለሁ። ፖለቲካዊ ጉዳይ ስናገር ደግሞ የሚያስደስታት ፖለቲካ ብቻ ነዉ ይባላል።»

አንጌላ ሜርክል ወደፖለቲካዉ ዘግይተዉ ነዉ የመጡት፤ ታቅዶ ሳይሆን እንደዕድል። በጎርጎሪዮሳዊዉ 1994 የቀድሞዉ የምስራቅ ጀርመን ጠቅላይ ሚኒስትር ሎታር ደ ሚዜር ምክትል ቃል አቀባይ የነበሩት የያኔዋ የ35ዓመት ወይዘሮ የተግባቦት ችሎታቸዉን በሂደት አዳበሩ። በዘመነ መራሄ መንግስት ኮኽል የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትር ሆኑ።

Angela Merkel CDU Vorsitz

ሜርክል CDU ሊቀመንበር ሆነዉ ሲመረጡ

ቦታዉ በፊዚክስ የዶክትሬት ዲግሪ ላላቸዉ ምሁር ተገቢ ነበር። በዚሁ የዘመን ቀመር በ1998ዓ,ም የፌደራል ጀርመን ምርጫ ክርስቲያን ዴሞክራት ሲሸነፍ ፓርቲዉ እጅግ ተደናገጠ። አንጌላ ሜርክል ግን ፍንክች አላሉም። ይልቁንም ከኮኽል ዘመን በኋላ የራሳቸዉን ስፍራ በመያዝ የፓርቲዉ ዋና ጸሐፊ ለመሆን አጋጣሚዉን እንደመልካም እድል ተጠቀሙበት። ከዚያም ለፓርቲ በተሰጠ ክፍያ የተፈጠረ የቅሌት ተግባርን በመመርመር የቀድሞዉን መራሄ መንግስት ዉድቀት አፋጠኑት። ላለፉት 13ዓመታት ሜርክል CDUን ይመራሉ፤ ለስምንት ዓመታትም መራሂተ መንግስት ናቸዉ፤ በፓርቲዉ ዉስጥም እገሌ ከእገሌ ሳይባል የሚቃወሟቸዉን ሁሉ ባዷቸዉን እንዲጓዙ አድርገዋል። የአመራር ችሎታቸዉንም በገሃድ አሳይተዋል። ችግሩ ግን ወዴት የሚለዉ ነዉ? ይህም በክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት የሚገኙ ብዙዎች የሚጠይቁት ጥያቄ ነዉ። አሁን ፓርቲዉ አቅጣጫዉ ወዴት ነዉ በሚል ከዉስጥ የሚሰነዘር ክስ አለ። እሳቸዉም ፓርቲያቸዉ ዉስጥ አይነኬ ሆነዋል። ጋዜጠኛ ራልፍ ቦልማን እንደሚለዉ ይህ የፓርቲዉ ረጋ ያለና ተጨባጭ ሁኔታን ከሚከተል ባህርዩ የመነጨ ነዉ። «ሜርክል እስከተሳካላቸዉ ድረስም ይህ እንዲህ ይቀጥላል።»

ያኔተ ዛይፈርት

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic