የሜርክል የደስታ መግለጫ ለዶክተር አብይ | ኢትዮጵያ | DW | 05.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሜርክል የደስታ መግለጫ ለዶክተር አብይ

ሜርክል ለአዲሱ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ከባድ ፈተናዎችን ማለፉ እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል።

አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ቀውስ ይወጣሉ ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ፖለቲካዊ ውይይት ያካሂዳሉ ብለው  ተስፋ እንደሚያደርጉ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል  አስታወቁ ። ሜርክል ለዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት ሀገሪቱ የተጋረጡባትን ከባድ ፈተናዎችን ማለፉ እንዲሳካላቸው ተመኝተዋል። ለረዥም ጊዜ የዘለቀው የሁለቱ ሀገራት የቅርብ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎታቸው መሆኑን ያሳወቁት ሜርክል በደስታ መግለጫቸው መንግሥታቸው ለብልጽግና እና ለተጨማሪ ነጻነት ጉዞ ላይ የምትገኘውን ኢትዮጵያን ይደግፋል ብለዋል።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች