የሜርክል የአፍሪቃ ልማት እቅድ እና ትችቱ | አፍሪቃ | DW | 14.06.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የሜርክል የአፍሪቃ ልማት እቅድ እና ትችቱ

የአፍሪካ መሪዎች - አሁኑኑ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር እጃቸው እንዲገባ ከጀርመን መንግሥት ይጠብቃሉ ፡፡ ሁሉም የአፍሪካ መሪዎች፣ እነሱ በነደፉት በ2063 አጀንዳ ላይ ተመሥርታችሁ“ ፍርዳችሁን በእኛ ላይ ስጡ ብለው እስከ መማጸን ድረስ ሄደዋል፡፡ ይህን ሲሉ፣ ሌሎች ቅደመ ሁኔታዎችን አሟሉ“ ብላችሁ ከእንግዲህ አትጠይቁን ማለታቸው ነው፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:05

የሜርክል የአፍሪቃ ልማት እቅድ እና ትችቱ

 

የጀርመን የልማት ተራድኦ ሚኒስትር ለአፍሪቃ ልማት የነደፉት የማርሻል ፕላን የተባለው እቅዳቸው ትናንት እና ከትናንት በስተያ በርሊን ውስጥ በተካሄደው የቡድን ሀያ እና የአፍሪቃ ጉባኤ ላይ የሜርክል እቅድ የሚል ስያሜ ተስጥቶታል። በጉባኤው ላይ እንደተገለጸው በአዲሱ እቅድ ከዚህ ቀደም ለአፍሪቃ ይሰጥ የነበረው የልማት እርዳታ ይለወጣል። የዶቼቬለው ክላውስ ሽቴከር በጉዳዩ ላይ በጻፈው ሀተታ እንዳለው  እቅዱ ጥሩ ጅምር ነው። ይሁን እና ይህና ቡድን ሀያ መፍትሄ ብሎ ያቀረበው እቅድ የክፍለ ዓለሙን ችግር በአንዴ ሊፈቱ አይችሉም ፡፡  ከ1960 ዓ.ም. እ.አ.አ. እስከ አሁን ድረስ ለአፍሪካ መንግሥታት „ይታደል „ የነበረው የገንዘብ ዕርዳታ፣ አሁን መቆሙን የትላንትናው ስብሰባ ውጤት ግልጽ አድርጎአል፡፡4000 ቢሊዮን ዶላር እስከ ዛሬ ድረስ እዚያ ፈሶ ፣…የት እንደ ገባ ፣…ማን እንደበላው ሳይመረመርና ሳይታወቅ፣አንዳች ውጤትም ለሕዝቡ ሳያመጣ ፣እዚያው ቀልጦ ፣ያን ያህል ብር አፍሪካ ውስጥ ጠፍቶአል፡፡ በዕድገትም ሆነ በዓለም ገበያም ላይ ፣ የአፍሪካ ተሣትፎ - ከፍ ሳይል ፣እንዲያውም ብሶበት-  ምሥጢር አይደለም- ወደ ታች እያሽቆለቆለ ሄዷል፡፡ ያለፈው አሠራር ዕድገት ሳይሆን ውድቀትን በአፍሪካ አስከትሎአል፡፡ አሁን በአገራቸው ውስጥ ለውጥ ለማምጣትና- ጀርመኖች እዚህ እንደሚሉት „…ሪፎርም ለማወጅ ዝግጁ“ ለሆኑ መንግሥታት በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ለመስጠት እነሱ ወስነዋል፡፡ 
ዜናው ጥሩ ነው!
ለውጭ ከበርቴዎችም፣ እዚያ አፍሪካ ወርደው ገንዘባቸውን አፍስሰው ለመሥራት ለሚፈልጉ ባለጸጋዎችም „…አመች የሥራ ዕድል ለመክፈት“ ፈቃደኛ ለሆኑ የአፍረካ መንግሥታት፡ - ለእነሱ ብቻ „ቅድሚያ“ ሰጥቶ እነሱን ለመርዳት ጀርመኖች ወስነዋል፡፡
ይህም የማይናቅ ትልቅ ዜና ነው!
ዓላመው በዚህ እርምጃ „…አገሩንና መንደሩን ጥሎ“ ለመሰደድ ቆርጦ አሁን የተነሳውን ትውልድ- የሥራ ዕድል  እዚያው በመክፈት

GMF | Claus Stäcker

ክላውስ ሽቴከር

እነሱን እንዳይወጡ ማስቀረት ይቻላል ብለው ጀርመኖች ገምተዋል፡፡ በዚህ አመት ብቻ ! ወደ 400.000 የሚጠጉ የአፍሪካ ስደተኞች እዚህ አውሮፓ ይገባሉ ብለው  ጀርመኖቹ ሠግተዋል፡፡  በመጪው አሥራ አምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ደግሞ፣ ቁጥራቸው ከፍ ብሎ ወደ 440 ሚሊዮን የሚጠጉ የአፍሪካ ወጣቶች „..የሥራና የዳቦ ጥያቄ “ አንስተው፣ መልስ ከአላገኙ መንደራቸውን  ይለቃሉ ብለው ተጨንቀዋል፡፡ ስለዚህ በየአመቱ ለሃያ ሚሊዮን ወጣት፣ የሥራ ዕድል እዚያው አፍሪካ ውስጥ ለመክፈት ሁኔታው መመቻቸት አለበት፣ በሚለው መሰረተ ሓሳብም ላይ - በርሊን ላይ እንደተሰማው ሁሉም ወገኖች ትላንት ተስማምተዋል፡፡ 
አይቮርኮስተና ሞሮኮ፣ሩዋንዳና ሴንጋል፣ እንዲሁም ቱኒዚያ፣ የመጀመሪያው የፕላኑ ተጠቃሚ ሁነው በርሊን ላይ ተመርጠዋል፡፡  ግን! እዚህ ላይ የሚያስቀው  - በአሁኑ ሰዓት - የሚገርመው፣ የአገራቸውን ችግር ለመፍታት ሥልጣን የወጡት የአፍሪካ መሪዎች የወጣቱን ትውልድ ጥያቄ ከአውሮፓ ጋር ሲነጋገሩ „…ትርፍ አምጪ …ገንዘብ መሰብሰቢያ…“ አርዕስት የወጣቱን ችግር እነሱ አድርገው ሰው ፊት ይህን ዓይነት አቋም ይዘውእዚህ ሲቀርቡ፡-  ክላውስ ሽቴከር- በሐተታው ላይ እንደ ጻፈው ፣ በጣም ያሳዝናል ይላል፡፡
ሳያፍሩበት በዚህ ዘዴም - የአፍሪካ መሪዎች - አሁኑኑ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር እጃቸው እንዲገባ ከጀርመን መንግሥት ይጠብቃሉ ብሎም በአሽሙር ስማቸውን ያነሳል፡፡ 
ሌላም ነገር በርሊን ላይ ተሰምቶአል፡፡
ሁሉም የአፍሪካ መሪዎች፣ እነሱ በነደፉት በ2063 አጀንዳ ላይ፣በዚያ ላይ „ ተመሥርታችሁ“ ፍርዳችሁን በእና ላይ ስጡ  ብለው እስከ መማጸን ድረስ ሄደዋል፡፡ በሌላ አነጋገር -ይህን ማለታቸው፣ ሌሎች ቅደመ ሁኔታዎችን „…አሟሉ“ ብላችሁ ከእንግዲህ አትጠይቁን ማለታቸው ነው፡፡  በዚህ አካሄድ ደግሞ እንደ ሩዋንዳ ያሉ አምባገነን መንግሥታት፣…ወይም ደግሞ የቻይናን ጎዳና እንደ ጌጥ፣ የእሱዋንም ሞዴል እንደ ትልቅ ነገር እኛ እንከተላለን የሚሉ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የአፍሪካ መንግሥታት ምንም ዓይነት ጥያቄ አታንሱብን ባይ ሁነዋል፡፡

ከእነሱም ጋር ሌሎች አስቸጋሪ አገሮች አሉ፡፡
ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዳይሳልፉ ጀርመንና የአውሮፓ ሕብረተሰብ አንድ ላይ ሁነው ከእነሱ ጋር አብረው ለመሥራት ጥረት የሚያደርጉት እንደ ሱዳንና እንደ ኤርተራ ያሉ አስቸጋሪ አምባገነን መንግሥታትም መረሳት የለባቸውም፡፡ አዲሱን „የሜርክል ፕላን“ በሥራ ላይ ለማዋል ፣ እነዚህ መንግሥታትና  አገሮች ሁሉ - ይህን አድርጉ፣ ያን አሟሉ ብሎ እነሱን የሚጠይቃቸውን ሰው ማየት አይፈልጉም፡፡እንዲያውም አንዱ ያለው የሚገርም ነው፡፡ „…በሉ እንግዲህ ገንዘቡን ቃል እንደገባችሁልን ሳታዘገዩ ቶሎ ብላችሁ አስተላልፉልን“ የሚለው የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት የ ፖል ካጋሜ ንግግር - በጣም ይገርማል- ከዚሁ ሁኔታ የመነጨ ነው፡፡
„….አምስቱን የአፍሪካ መንግሥታት አስቀድማችኋል፡፡ አርባ ሰባቱን ደግሞ ሳትረሱ ቶሎ በሉ ፣ ተጣደፉ እንጂ..“ የሚለው የአፍሪካ መሪዎች አነጋገሪም እንደዚሁ እጅግ የሚገርምም የሚያሳዝንም ጉዳይ ነው፡፡
ግልጽ ለመሆን፡- 
በአህጉሪቱ በትልቁዋ አፍሪካ ፊት የተደቀኑትን  ችግሮች፣ ለመፍታት ዕውነቱን ለማነገር „…ማርሻ ፕላን „ ሆነ „የ ቡድን 20 አገሮች መፍትሔ“ ወይም  ደግሞ አሁን አዲስ ስም የያዘው „ የሜርክል ፕላን„ አንዱም ሆነ ፣ ወይም ሁሉም አንድ ላይ ተጨፍልቀው፣ በቀላሉ  ብዙዎቹ እንደሚያስቡት፣የአህጉሪቱን ችግር በአንዴ የሚፈቱ  መድሓኒት አይደሉም ፡፡ ይልቅስ የእድገትና የልማት ሚኒስትሩ ሚስተር ጌርድ ሙለር እንደአሉት „…ሁሉ ነገር ከእያንዳንዱ ነገር ጋር የተያያዘና የተቆላለፈ ፣የተሣሰረ መሆኑን መረዳትና መገንዘብ በአሁኑ ሰዓት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡“ ያሉትን ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡  „…የሜርክል ፕላን „ አዲስና ጥሩ ጅምር ነው፡፡ ከዚያ አልፎ ግን ይህን በሥራ ላይ ለመዋል የአውሮፓን አንድነትን ማህበረሰብን ፣የአባሎቹን ሕብረትና የሌሎቹንም መንግሥታት ድጋፍን የሚጠይቅ እርምጃ ነው፡፡ የአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ሚስተር ዶናል ትራምፕና እና የጂ 20 አባል አገር መሪዎች ፣ በዚህ አቅጣጫም ምን እንደሚያስቡ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡  ይህ ከሆነ ደግሞ የ“….ሜርክልን „ አዲሱን ፕላን ለመጪው ክፍለ -ዘመን፣ እንደ መነሻ መሠረት አድርጎ መውሰዱ ለጊዜው በቂ ይመስለናል፡፡

ክላውስ ሽቴከር/ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic