የሜርክል የአሜሪካን ጉብኝት | ዓለም | DW | 01.05.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሜርክል የአሜሪካን ጉብኝት

የጀርመን መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከነገ ጀምሮ አሜሪካን ይጎበኛሉ ። የሜርክል የአሁኑ ጉብኝት ከከዚህ ቀደሞቹ የአሜሪካን ጉብኝቶች በተለየ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚካሄደው ።

ሜርክል አሁን ዩናይትድ ስቴትስን የሚጎበኙት የአሜሪካ ብሔራዊ የስለላ ድርጅት የርሳቸውን ስልክ ሳይቀር መሰለሉ ሁለቱን ሃገራት ብዙ ካነጋገረ በኋላ ነው ። የዩክሬኑ ቀውስ መፍትሄ ፍለጋም የሁለቱ ሃገሮች የወቅቱ ትኩረት ነው ።
የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ስቴትስ ያካሄዷቸው ጉብኝቶች ይበልጥ አስደሳች ነበሩ ። በአሜሪካን ምክር ቤት ውስጥ ያሰሙት ንግግር ወይም አሜሪካን የሸለመቻቸው የነፃነት ሜዳልያ የትናንት ትውስታዎች ናቸው ።በአሁኑጉብኝት ግን የሚስተናገዱት ባዕድ መስለው በታዩትና በተለያዩ ቀውሶች በተወጠሩት መሪ ነው ። የአሜሪካ ብሄራዊ የስለላ ድርጅትአካሄደባቸው ከተባለው ስለላ በኋላ የዩክሬን ቀውስ ተከትሏል ። በሜርክል የአሁኑ የዋሽንግተን ጉብኝት ትልቁ የመነጋገሪያ አጀንዳ የዩክሬን ቀውስ ነው የሚሆነው ። ይህ ደግሞ የዋሽንግተኑ የስልታዊና ዓለም ዓቀፋዊ ጥናቶች ማዕከል በምህፃሩ (ሲ ኤስ አይ ኤስ) ባልደረባ ሂተር ኮንሊ በትክክለኛ ጊዜ የሚነሳና ጠቃሚም ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል ።
«ይህ ውይይት በሚያስገርም ሁኔታ ወቅታዊና እጅግ አስፈላጊ ነው።እነዚህ ሁለቱ መሪዎች ምዕራቡ

ዓለም በሩስያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ በአስደናቂ ፍጥነት ፍፃሜው ላይ በደረሰበት ወቅት ነው የሚገናኙት።አዲስ ፖሊሲ እንደገና መቀረፅ ይኖርበታል።ስለዚህ እነዚህ ሁለት መሪዎች በዚህ ላይ ማትኮራቸው ና ይህን አዲስ የፖለቲካ መርህ በመቅረፅ ረገድ የጀርመን ሚና ለስኬታማነቱ ወሳኝ ነው። »
ለዩክሬኑ ችግር መፍትሄ ፍለጋ ከሁለቱ ሃገራት ብዙ ይጠበቃል ። ይሁንና አውሮፓውያን አጋሮች በሩስያ ላይ አዲስ የማዕቀብ እርምጃዎችን ለመውሰድ አንድ ሳምንት ያህል ማስጠበቃቸው አሜሪካውያኑን ማበሳጨቱ አልቀረም። ሄሪቴጅ በተባለው የጥናት ድርጅት የአውሮፓ ጉዳዮች አዋቂ ኒል ጋርዲነር እንደሚሉት በዩክሬን ምክንያት የጀርመንና የአሜሪካን ግንኙነት እንደገና ለአደጋ የመጋለጡ ስጋት አለ ።
« የሩስያ ጉዳይ እንዴት መያዝ እንደሚገባው በበርሊንና በዋሽንግተን መካከል ሰፊ ልዩነት አለ ። ፕሬዝዳንት ኦባማ በሩስያ ላይ ጠንካራ አቋም እንዲይዙ ተጫማሪ ጫናዎች ይደረጉባቸዋል ።እንደሚመስለኝ ዩናይትድ ስቴትስ በሩስያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ አጠናክራ ትቀጥላለች ። ጀርመኖች ደግሞ በተለያየ ምክንያት ይህን ለማድረግ የሚያወላውሉ ይመስለኛል ። ስለዚህ እዚህ ላይ ትልቅ ልዩነት አለ ። የዩክሬን ጉዳይ ጀርመንንና ዩናይትድ ስቴትስን ይበልጥ የማራራቅ ኃይል ያለው ይመስለኛል ። »
በጋርዲነር አስተያየት ይህ የአሜሪካንና የጀርመንን ግንኙነት አደጋ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ ነው ። ከዚህ

ሌላ የአሜሪካን ብሔራዊ የስለላ ድርጅት ባካሄደው ስለላ ምክንያት የጀርመን ፖለቲከኞች በአሜሪካን ላይ ያላቸውን ቅሬታ ቢሰነዝሩም አሜሪካኖቹ ቦታም እንደማይሰጡት ነው ተንታኙ ጋርዲነር የተናገሩት ።
« ጀርመንና ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት ሩስያን በተመለከተ ሲያራምዱ የቆዩት የሰላም መርህ ነው ። ይህ የሆነውም የኃይል ምንጮች አቅርቦት ጥገና በመሆናቸው ነው ። ይህ ደግሞ በጀርመን በሃገር ውስጥ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ። እዚህ ዋሽንግተ ግን ይህ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ። የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር የጀርመን ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከNSA ጋር በተያያዘ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች የሚያጎበድዱ አይመስለኝም ። »
የጀርመን ማርሻል ፈንድስ የተባለው ድርጅት ሃላፊ ካረን ዶንፍሪድ ደግሞ ስለ ሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ያላቸው አስተያየት የተለየ ነው ።
« የጀርመንና የአሜሪካንን ግንኙነት በተለየ ሁኔታ ነው የምመለከተው ። ግንኙነት እጅግ ጠንካራ ነው ። ባለፉት ዓመታትም ጠንካራ ግንኙነት ነበረ ብዬ አምናለሁ ።በእርግጥ የNSA ጉዳይ እጅግ አስቸጋሪው ምዕራፍ ነበር ። ሆኖም በዩክሬኑ ቀውስና የኢራንና የሶሪያን ችግር በመሳሰሉት ጉዳዮች ምን ያህል በቅርበት እንደምንሰራ ማየት ይቻላል ።

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic