የማዕከላዊ  ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች እየተመለሱ ነው  | ኢትዮጵያ | DW | 08.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የማዕከላዊ  ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች እየተመለሱ ነው 

ክልሉ እንዳስታወቀው እስካሁን ወደ ቀያቸው የተመለሱት ቁጥር ከ13 ሺህ በላይ ነው። በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በአማራና በቅማንት ማኅበረሰብ መካከል በዚህ ዓመት በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉት ሰዎች የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንም የክልሉ የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታውቋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:54

ለተፈናቀሉት የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ ነው።

ከአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተፈናቀሉ ሰዎች ወደቀያቸው እየተመለሱ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስትና የየአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ክልሉ እንዳስታወቀው እስካሁን ወደ ቀያቸው የተመለሱት ቁጥር ከ13 ሺህ በላይ ነው። በምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በአማራና በቅማንት ማህበረሰብ መካከል በዚህ ዓመት በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉት ሰዎች የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑንም የክልሉ የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ማስተባበሪያ ኮሚሽን አስታውቋል። በግጭቱ በሁለቱም ዞኖች ህይወት ጠፍቷል፣ ከ6000 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ ዓለምነው መኮንን ከባሕር ዳር ዝርዝር ዘገባ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ 

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች