የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ሰላም | አፍሪቃ | DW | 05.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ሰላም

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን እንዳስታወቀዉ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ዛሬም በቀጠለዉ ዉጊያ የተገደሉ የአስራ-ስድስት ሰዎች አስከሬን በከተማይቱ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ተከማችቷል።

የአፍሪቃ ሕብረትና ፈረንሳይ ሥርዓተ-አልበኝነት ወደ ነገሰባት ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት እንዲያዘምቱ የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ወሰነ።ምክር ቤቱ ዛሬ በአብላጫ ድምፅ ባፀደቀዉ ዉሳኔ መሠረት ፈረንሳይ አንድ ሺሕ ሁለት መቶ ወታደሮችን ሰሞኑን ታዘምታለች። የአፍሪቃ ሕብረትም ወታደሮች ለማዝመት መዘጋጀቱን አስታዉቋል።እዚያዉ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ርዕሠ-ከተማ ባንጉይ ዉስጥ ተቀናቃኝ ሚሊሺያዎች በገጠሙት ዉጊያ በርካታ ሰዎች መገደላቸዉ ተዘገቧል።ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን እንዳስታወቀዉ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ ዛሬም በቀጠለዉ ዉጊያ የተገደሉ የአስራ-ስድስት ሰዎች አስከሬን በከተማይቱ በሚገኙ ሁለት ሆስፒታሎች ተከማችቷል።የተለያዩ የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ደግሞ በርዕሠ-ከተማይቱ በሚገኝ አንድ መስጊድ እና ባካባቢዉ ከሰማንያ በላይ አስከሬን ተዘርሯል።ባጠቃላይ ከተማይቱ ዉስጥ የተገደለዉ ሰዉ ቁጥር ከአንድ መቶ እንደሚበልጥም ተዘግቧል።የሳሌካ አማፂያን የቀድሞዉን የሐገሪቱን መንግሥት ባለፈዉ መጋቢት ከስልጣን ካስወገዱ ወዲሕ ደኸይቱ አፍሪቃዊት ሐገር በወሮበሎች ጥቃት እና በታጣቂዎች ዉጊያ በርካታ ሰዉ ይገደልባታል።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ