ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የትግራይ ባለሥልጣናት ከ4 ሺህ በላይ የጦር ምርኮኞች ለቀናል ማለታቸዉን የፌዴራል መንግሥት አስተባብሏል። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ እንደተናገሩት "በተለያየ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል ውስጥ ለሥራ ፍለጋ የሄዱ፣ እና ሕወሓት በአፋርና በአማራ ክልሎች ተቆጣጠራቸው በነበሩ አካባቢዎች የያዛቸው ናቸው " ብለዋል።
የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ኃይሎች ተቆጣጥረውት ከቆዩባቸው የአፋር ክልል፤ ዞን ሁለት፤ ስድስት ወረዳዎች መውጣታቸውን ቢገልጹም፤ የአከባቢው ነዋሪዎች እና የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ጉዳዩን አስተባብለዋል። የሕወሓት ኃይሎች በአንዳንድ የአፋር ቀበሌዎች እንደሚገኙ እና የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ትግራይ ክልል ከገቡ 20 ርዳታ የጫኑ መኪኖች ሌላ የደረሰ ርዳታ እንደሌለ በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሚመራው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ዐስታወቀ። ከረዥም የውዝግብ ጊዜ በኋላ 20 ሰብአዊ ርዳታ የጫኑ መኪኖች መቐለ የደረሱት ባሳለፍነው ዓርብና ቅዳሜ ነበር።
የሰብዓዊ መብት ድጋፍ ያለምንም ገደብ እና መደናቀፍ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። ይሁንና የድጋፍ ሰጪዎች እጥረት እና በመላው ኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር መብዛት ሰብዓዊ ድጋፍ በተሟላ ሁኔታ ለማድረስ እክል መፍጠሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።