የማንዴላ ድርሻ ለሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ፤ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 18.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የማንዴላ ድርሻ ለሳይንስና ሥነ-ቴክኒክ፤

የደቡብ አፍሪቃን ፀረ የዘር መድልዎ ሥርዓት (አፓርታይድ) በመታገል ህዝቡ ለድል የበቃው፤ በሕይወት ቢኖር ኖሮ በዛሬዋ ዕለት 67ኛ ዓመቱን ማክበር ይችል በነበረው ስቲቭ ቢኮን በመሳሳሉ የጥቁሩን ሕዝብ ንቃተ ሕሊና ከፍ ለማድረግ ዘመቻ ባካሄዱ ጠንካራ

ታጋዮችና በበላይ መሪአቸው ኔልሰን ማንዴላ አይበገሬነት መሆኑ የሚካድ አይደለም። ስለ ኔልሰን ማንዴላ የነጻነትና እኩልነት ትግል ብዙ ተብሏል። ትምህርት በተለይ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲስፋፋ ምን ዓይነት ድርሻ አበርክተዋል? የዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ዝግጅት የሚያተኩርበት ርእስ ነው«የአንድ አገር /ዕድገት /መለኪያ ልጆችን እንዴት አድርጎ በትምህርት ፤ በሁሉም ነገር ማሳደግ ነው»።

ከኔልሰን ማንዴላ ንግግሮች ፣ በግርድፉ የተወሰደ ጥቅስ ነው። እጅግ ታዋቂው የፀረ መድልዎ ሥርዓት አፓርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ፤ ኀሙስ ኅዳር 26 ቀን 2006 ካረፉ በኋላ፣ ባለፈው እሁድ ግብዓተ-መሬት እስኪፈጸም ድረስ በዓለም ዙሪያ መገናኛ ብዙኀን ስለእኒህ ሰው ጠንካራ ተጋድሎ ፣ ይቅር ባይነት፤ የዜጎች እኩልነትና አንድነት ፤ ስለቆሙለት ጽኑ ዓላማ ፤

በአጠቃላይ ከልደት እስከ ሞት ታሪካቸውን ፤ ገድላቸውን በሰፊው ሲያሰሙ፣ ሲያቀርቡ ነበረ የሰነበቱት። 27 ዓመታት ከመታሠራቸው በፊት ህግ ተምረው ጠበቃ በመሆን ይሠሩ የነበሩት ማንዴላ ስለትምህርት ፣ በተለይም ስለ ሳይንስና ሥነ ቴክኒክ የነበራቸው አመለካከት እንዴት ይታወሳል? (ይቀጥላል)

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

Audios and videos on the topic