የማንዴላ ሞትና የዓለም አስተያየት | ዓለም | DW | 06.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የማንዴላ ሞትና የዓለም አስተያየት

ዓለም፥ ድፍን ዓለም የሩሲያዉ ፕሬዝዳት ቭላድሚር እንዳሉት «የዘመኑን ታላቅ ፖለቲከኛ» በማጣቱ ተከዘ።አብዛኛዉ ዓለም አዘነ።ደቡብ አፍሪቃዎች ደግሞ በሐገሪቱ ፕሬዝዳት በጄኮብ ዙማ አገላለፅ «መሆን የሚፈልጉትን እንዲሆኑ ባደረጓቸዉ» ታላቅ ሰዉ ሞት አረገዱ።

ማንዴላና ደቡብ አፍሪቃ

ማንዴላ።ከእንግዲሕ እኛ የደቡብ አፍሪቃ ታላቅ ልጅ፥ እኛ የዴሞክራቲክ ሥርዓቷ ቀንዲል፥ እኛ የደቡብ አፍሪቃዉያን ልዩ አባት ታላቅ ምግባራቸዉ ነዉ-ቀሪ፥ መዘከሪያቸዉ።እንደገና ሒሩት መለሰ ያጠናቀረችዉን ተክሌ የኋላ ያሰማናል።

ማንዴላና ኢትዮጵያ

ከሃያ ሠባት ዓመታት እስራት በሕዋላ በ1982 እንደተፈቱ ቀድመዉ ከጎበኟችዉ ሐገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነበረች።ኢትዮጵያን ከብዙ ሐገራት አስቀድመዉ የጎበኙበት ብዙ ምክንያት ሊኖራቸዉ ይችላል።ዋናዉ ግን ከመታሰራቸዉ በፊት እንደ ወጣት ታጋይ የሽምቅ ዉጊያ የተማሩባት ሐገር በመሆኗ ነዉ።በ1982 አዲስ አበባ ሲገቡ «ሰዉ እንደነበርኩ ያወቅሁባት» ብለዋት ነበር ኢትዮጵያን።ኢትዮጵያዉያንስ ዛሬ ምን አሉ።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጥቂት አስተያየቶችን አስባስቧል።

ማንዴላና የኢትዮጵያ መንግሥት

Äthiopien - Premierminister Haile Mariam Desalegne

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

 

የኢትዮጵያ መንግሥት በኔልሰን ማንዴላ ሞት በመላዉ ሐገሪቱ የሚፀና የሐዘን ቀን ለማወጅ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የመንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማልን ጠቅሶ ዘግቦልናል።በሐዘኑ ጊዜ መደረግ ያለበትን ዝር ዝር ጉዳይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይወስናል ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ።ፓሪስ ጉባኤ ላይ የሚገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ለደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝዳት ለጄኮብ ዙማ የሐዘን መግለጫ መላካቸዉን እዚያዉ ፓሪስ የሚገኙት የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸዉ ረዳ በስልክ ገልፀዉልናል።

ማንዴላና የአፍሪቃ ሕብረት

 

የአፍሪቃ ሕብረትም ማንዴላን በመጪዉ ዕሁድ አዲስ አበባ ዉስጥ በልዩ ሥርዓት ለመዘከር አቅዷል።የሕብረቱ ምክል ሐላፊ ኤራቱስ ሙዮንቻ ዛሬ በሠጡት መግለጫ የታላቁ አፍሪቃዊ ፖለቲከኛ ሞት ለመላዉ አፍሪቃዉያን አሳዛኝ መሆኑን ገልፀዋል።ሙዮንቻ እንዳሉት ማንዴላ ለአፍሪቃዉያን ሁሉ የመቻቻል፥ የመዋሐድ፥ የፀረ-ዘረኝነት አብነት ነበሩ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ አጭር ዘገባ ልኮልናል።

Merkel bei Mandela in Johannesburg Archiv 06.10.2007

ማንዴላ ና ሜርክል

 

ማንዴላ፤ ጀርመንና የአዉሮጳ

ኔልሰን ማንዴላ ለጀርምንዋ መራሒተ-መንግሥት ለወይዘሮ አንጌላ ሜርክል የዲሞክራሲያዊ ሞራል ፅናት አብነት ናቸዉ።ሜርክል ዛሬ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ እንዳሉት ማንዴላ «የሞራል ፅናት ከጠመንጃ ጠንካራ ሐይል እንደሚበልጥ ለመላዉ ዓለም ሕዝብ ያስመሰከሩ» ታላቅ ሰዉ ናቸዉ።የጀርመኑ ፕሬዝዳት ዮአኺም ጋዉክም የማንዴላን ትግል፥ ትዕግሥትና ፅናት አድንቀዋል።ሒሩት መለሰ የጀርመንና የአዉሮጳ መሪዎችን አስተያየት አሰባስባለች።

 

Barack Obama Mimik zerknirscht abwehrend ernst

ኦባማ

ማንዴላና ዩናይትድ ስቴትስ

ለዩናይትድ ስቴትስ፥ ለብሪታንያ እና ለተከታዮቻቸዉ መንግሥታት በተለይም ለወግ አጥባቂ ፖለቲከኞቻቸዉ ማንዴላና ማንዴላ ይመሩት የነበረዉ የደቡብ አፍሪቃ የአፍሪቃዉያን ብሔራዊ ምክር ቤት (ANC) አሸባሪ ነበሩ።ኋላ ግን ማንዴላ የመቻቻል፥ የእኩልነት፥ የፍትሕ ምሳሌ ሆኑ።ዛሬ ሲሞቱ ደግሞ ድሮ በአሸባሪነት የሚወነጅሏቸዉ ሪፐብሊካኖችም፥ በነፃነት ታጋይነት የሚያደንቋቸዉ ዴሞክራቶችም እኩል አድንቀዉ አወድሰዋቸዋል።የዋሽግተኑን ወኪላችንን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግረነዋል።

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ጃፈር አሊ

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አበበ ፈለቀ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic