የማኅበራዊ ፍትኅ መታሰቢያ ዕለት፤ | ዓለም | DW | 20.02.2013
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የማኅበራዊ ፍትኅ መታሰቢያ ዕለት፤

ዓለም አቀፉ የማኅበራዊ ፍትኅ ቀን በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል። ይህን ዕለት መንስዔ በማድረግ ጀርመናዊው የማኅበራዊ ኑሮ ባለሙያ ዳንኤል ሽራድ-ቲሽለር ፤ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አገሮች፤ አዳጊ አገሮችን በማቆርቆዝ ፣ የራሳቸውን ኑሮ የተደላደለ ሊያደርጉ

አይገባም  ሲሉ አስገንዝበዋል። እንደ ሻራድ- ቲሽለር አስተያየት ፣ ለፍትኃዊ የማኅበራዊ ኑሮ ፤ ድኅነትን መቅረፍና ትምህርትን ማስፋፋት ወሳኝነት አላቸው። 

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ፤ ፍትኀዊ የማኅበራዊ ኑሮ፣ በኤኮኖሚ መዳከም ፤ በፋይናንስ ቀውስና በመሳሰለው ዝንዝር መራመዱ ቀርቶ ማሽቆልቆሉ ነው የሚነገረው።ለመሆኑ ፍትኀዊ የማኅበራዊ ኑሮ ሲባል ምንድን ነው፣  ዋና መሠረቶቹስ ምንድን ናቸው? ሄር ዳንኤል ሽራድ-ቲሽለር---

«ማኅበራዊ ፍትኅ ማለት ወይም ማኅበራዊ ፍትኅ የሚሠ።ምረው፤ ሁሉም ሆነ ማንናውም ሰው፤ ምኞቱን፣ ጥረቱን ፍጹም ተግባራዊ ለማድረግ በኅብረተሰብ ውስጥ፣ በእኩልነት ዕድሉን ሲያገኝ ነው። ይህም ማለት፤ ሰዎች፣ ከግል ሰብአዊ ነጻነት በመነሳት፣ በህይወታቸው የሚሹትን በከፍተኛ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ ሲቻላቸው ነው። ለዚህም መንግሥትና ኅብረተሰብ፣ ለሁሉም ፣ ይህ  በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ዕድል በተግባር እንዲተረጎም ማብቃት ይጠበቅባቸዋል። »

ሰዎች እኩል ዕድል ያገኙ ዘንድ፤ የትኞቹ ቅድመ ግዴታዎች መሟላት ይኖርባቸዋል?

አዎ ፤ በባለሙያው አመለካከት፤ ሰዎች በድኅነት መማቀቅ የለባቸውም። ከዚህም ባሻገር፤ መንግሥት፤ የኅብረተሰቡ አንድ አካል እንደመሆኑ  መጠን፣ የትምህርት ዕድል ለሁሉ እንዲዳረስ ማድረግ  ይጠበቅበታል። ገና በልጅነት ዕድሜ ተማሪዎች ዕድሉን እንዲያገኙ የሚያስፈልገው  ገንዘብም ቢሆን ሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል። በዚህ ረገድ የተካሄዱ ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ፣ ልጆች በልጅነት በትምህርት ገበታ ላይ እንዲገኙ ማብቃቱ፤ ለሠመረ ማኅበራዊ ኑሮ፤ በሙያም ለማደግ አስተዋጽዖ አለው። ይህ ደግሞ ኅብረተሰቡን በመላ የሚጠቅም ነው የሚሆነው። መንግሥት፤ ለማኅበራዊ ፍትኅ ከቆመ፤ በኤኮኖሚም የተሻለ ዕድገትም ሆነ እመርታ የማሳየት ዕድሉ ከፍ ያለ ነው።

ዴሞክራሲ ፤ በትጋት የሚካሄድ ህዝባዊ  ተሳትፎ ፤ መሠረታዊ የማኅበራዊ ፍትኅ ዓምዶች ናቸው። ሰዎች ህይወታቸውን እንዴት እንደሚመሩ ፣ በፖለቲካም ረገድ አብሮ የመወሰን መብት ከሌላቸው መሠታዊው የማኅበራዊ ፍትኅ ይጓደልባቸዋል። 

በፖለቲካ አብሮ የመወሰን መብቱ እንዳለ ሆኖም በአንዳንድ ረገድ ከሀገር ሀገር ያለው አያያዝ ልዩንት ያመጣል። በዩናይትድ እስቴትስ፤ ባለፉት ዐሠርተ ዓመታት የተዛባ ሁኔታ ተከሥቷል። በአንድ በኩል ሰፊ ገቢ ያላቸው ፤ በማኅበራዊው ኑሮ ፍጹም የተደላደለ ህይወት ሲመሩ እጅግ ወደ ድኅነቱ እርከን የተገፉት ቁጥር ደግሞ አለቅጥ ነው, የጨመረው።  በድኅነት የተጎዱ ልጆችን በተመለከተ ፤በዓለም ውስጥ በኤኮኖሚ የመሪነቱን ቦታ ለያዘችው ሀገር ዩናይትድ እስቴትስ፤ አሳፋሪ ሆኖ ነው የሚታየው። የአንድ ልጅ የማኅበራዊ ኑሮ ይዞታ፤ ለወደፊቱ የተሳካ የትምህርት ደረጃ ወሳኝነት ያለው መሆኑ በዚያች ሀገር ጎልቶ ነው የሚታየው።

በተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ የተነደፈው የዓእማቱ ግብ ዋና ነጥብ ፣ ድህነትን ፈጽሞ  ማስወገድ እንኳ ባይቻል፤  መቅረፍ፣ ማለትም  ግማሽ በግማሽ መቀነስ ማለት ነው።

ድህነትን በመታገል ረገድ፣ ባለፉት ዓመታት  ከሞላ ጎደል እመርታ መታየቱ የሚካድ አይደለም በአማካይ ሲታይ ማለት ነው። እዚህ ላይ ኀላፊነት መሸከም ያለባቸው አዳጊ አገሮች  ብቻ አይደሉም። የምዕራባውያን ሀገራት የልማት ተራድዖ  ድርጅት፣ የአውሮፓው ኅብረት፤ እንዲሁም  የቡድን 20 አባል ሀገራት ፤ ሁሉም፤ በመላው ዓለም ድኅነትን  በመታገል  ረገድ ዐቢይ ኀላፊነት ያለባቸው መሆኑ ይታመንበታል።

የፍትኃዊ ማኅበራዊ ኑሮ ጉዳይ ባለሙያ ዶክተር ዳንኤል ሽራድ -ቲሽለር ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉ እንዲህ ብለዋል።

«በመሠረተ ሐሳብ  በኢንዱስትሪ የበለጸጉት ሃገራትቀጣይነት ላለው ዕድገት የጋራ ኀላፊነትመሸከም ይጠበቅባቸዋል። በእነዚህ አገሮች፤ ኑዋሪዎች፣ በሰፊው በማምረትና የሚመረተውንም ጥቅም ላይ በማዋል የተደላደለ ኑሮ ያላቸው ሲሆን፣ በዚያ ደረጃ ለመገኘት ለሚፍጨረጨሩትና ለሚጥሩት ታዳጊ አገሮች ዕድገት መሳካት አስተዋጽዖ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ይህም ሌሎችን ችግር ላይ ሳይጥል በጋራ ትብብር መከናወን ይኖርበታል።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 20.02.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17iEZ

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 20.02.2013
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/17iEZ