የማኅበራዊ ጉዳይ ተቆርቋሪና ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሠሠ | ባህል | DW | 26.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የማኅበራዊ ጉዳይ ተቆርቋሪና ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሠሠ

ሙዚቃን የጀመረዉ ገና ስምንተኛ ክፍል ሳለ ነዉ። የሙዚቃ  ፍቅሩን ለማሳደግ ከተወለደበት ከኢሊባቦር ጎር ተነስቶ  ወደ መሃል አዲስ አበባ መጥቶ ከባልንጀሮቹ ጋር «ዳሎል ባንድ»ን አቋቁሞ በመስራት ላይ ሳለ አብዮቱ ፈነዳ። ያኔ ታድያ የሙዚቃ ባንዱ ከአብዮት ሌላ የምዕራብ ቀመስ አይነት ሙዚቃን መስራት ተከለከለ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:59

ዘለቀ ገሠሠ

ሙዚቀኞቹ  ይህ ካልሆነማ ሙዚቃን በኮሌጅ ደረጃ ተምረን እንደዉም በድምቀት እናዜማለን ሲሉ አለሙ፤ ከሃገር ተሰደዱም። በጅቡቲ አድርገዉ ብዙ ዉጣ ዉረድን አይተዉ የማታ የማታ ልዕለ ሃያሊትዋ ሃገር አሜሪካ ችካጎ ገቡ፤ ከዝያም ይላል የዛሬዉ ታዋቂ ሙዚቀኛ የተፈጥሮ አካባቢ እና የማኅበረሰብ ጉዳይ ተቆርቋሪ ዘለቀ ገሠሠ ፤

«አሜሪካ እንደገባን ዩንቨርስቲ ገባን እኔ ሙዚቃ እና የንግድ ትምህርት መማር ጀመርኩ። ትምህርት ላይ ሳለሁ ካሊፎርንያ የኢትዮጵያን የአዲስ ዓመት በተዘጋጀዉ መድረክ ላይ ሄደን ታዋቂዉን አሜሪካዊ ሙዚቀኛ ስቲቪ ወንደርን አገኘነዉ። የአንድ ሪድዮ ጣብያ ባልደረባ የሆነች ኢትዮጵያዊት ልጅ ነበረች ያስተዋወቀችን። ሲቲቪ ወንደር የልምድ ሙዚቃ  ሰርቶልን እሱን ዓለም ላይ ለሚገኙ የሙዚቃ ኩባንያዎች ስንበትን፤ ከዚያ መካከል አንዱ ጃማይካ እነ ቦብ ማርሊ ቤተሰቦች እጅ ገባ፤ ከዝያ ታሪክ ሆነ ወደ ጀማይካም ጋበዙን በጎርጎረሳዉያኑ 1982 ዓ.ም የቦብ ማርሊን ልደት ሲያከብሩ ቦብ ማርሊ መቃብር ቦታ ዘፈንን። ቤተሰቦቹ ይህን ሙዚቃ አይተዉና ተማርከዉ ኮንትራት ሰጡን፤ ዳሎል ባንድ ዘ ጄኔቲክ የሚለዉን እነ ሰላም ሰላም እነ ሆያሆዬ ያሉበት ሙዚቃዎቻችንን እዝያዉ በቦብ ማርሊ ስቱድዮ ቀዳን። ሙዚቃ ዓልበሙ በዓለም ዙርያ ተበተነልን ከዝያ ይህን አይተዉ የቦብማርሊ ልጆች እናንተ ኢትዮጵያዉያን በመሆናችሁ ባህሉንም ለመማር ቀላል ስለሆነ አብረናችሁ መስራት እንፈልጋለንና ። ዚጊ ማርሊ ኤንድ ዘ ሜሎዲ ሜከርስ ከሚለዉ ጋር አብረን ተደባለቅን ከዝያ ታሪክ ሆነ ። ከነሱ ጋር ሁለት አልበሞች አብረን ሰራን ሁለቱም ግራሚ አሸንፈዉ በሚሊዮን አልበሞች ተሸጥዋል። »

ሙዚቀኛ ዘለቀ ገሠሠ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ ተመልሶ ተወዳጅ የሆኑ በተለይ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸዉን ሙዚቆችን አዉጥቶአል። የአካባቢ እና የማኅበራዊ ጉዳይ ተቆርቋሪም ሆኖ በተለያዩ ዘርፎች እያገለገለ ነዉ። ከዘለቀ ገሠሠ ጋር ያደረግነዉን ሙሉ ቃለ ምልልስ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።   

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic