ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በሰሜን ኢትዮጵያ ያንዣበበው የጦርነት ሥጋታ፤ የአማራ ክልል የልዩ ኃይል የቀድሞው ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ታፍኖ መሰወር እና መታሰር፤ እንዲሁም የአይንትራኅት ፍራንክፉርት የአውሮጳ ሊግ የዋንጫ ድልን በተመለከተ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች የተሰጡ አስተያየቶችን አሰባስበናል።
«እንኳን ጉዳት ሳያደርሱብህ ለልጆችህና ለቤተሰብህ በቃህ፤ ይህ አስተዳደር ከወያኔ አገዛዝ የባሰ ጨቋኝና ዘራፊ ይሆናል ብሎ ማንም ይከብዳል። ወንጀል የሰራ ለዚያውም ንፁኃን ፆመኞች ቀብር ላይ በሐዘን ላይ እያሉ የገደለን ህዝብ ተረባርቦ ፍትህ ካላሰጠ ፈጣሪን እፈራለሁ ቢል ውሸቱን ነው። የምን ዋጋ ማስተካከያ ነዉ። የዋጋ ጭማሪ ነዉ የሚባለዉ»
የኢድ አል-ፊጥር በዓል አዲስ አበባ ሲከበር አንድ ፖሊስ «በስሕተት» አፈነዳዉ የተባለ አስለቃሽ ጢስ መዕምናን ማስደንገጡና ማተራመሱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት 7.2 ሚሊዮን ቤቶች በ10 አመታት ለመገንባት የያዘው ውጥን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ነበሩ። የፕሬስ ነጻነት ቀን ሲከበር በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ጉዳይ ተነስቷል።
«ይህ ህመም የሙስሊሙ ብቻ አይደለም።ይህ ህመም የክርስቲያኑ ብቻም አይደለም።ይህ ህመም ለሰው ልጆች ክብር የሚጨነቁ የሚያስቡ ሁሉ ህመም ነው።»የሚል አስተያየት ስጥተዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ፤ ኦፌኮ እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን መግለጫ፣ የቅርስ ፈረሳ በአዲስ አበባ እንዲሁም የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያቀረቡት ወቀሳ በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ መነጋገሪያ የሆኑ ጉዳዮች ናቸው።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ስልጣን ከያዙ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አራት ዓመት ሞልቷቸዋል።ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓም አንስቶ በስልጣን ላይ ያሉት ዐብይ በአራቱ ዓመት የስልጣን ዘመናቸው በርካታ ለውጦች ቢያደረጉም ሀገሪቱ ግን ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን አስተናግዳለች።
መንግሥት ለሰብዓዊነት በሚል በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት የማቆም ውሳኔውን ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል። የመንግሥትን መግለጫ ተከትሎም በህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል አስተዳደር ውሳኔውን መቀበሉን አሳውቋል። ከሁለቱም ወገን የተሰማውን ግጭት የማቆም ውሳኔ ተከትሎም በርካቶች የተለያዩ አስተያየቶችን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አካፍለዋል።
በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ዝግጅታችን በኢትዮጵያና የምሥራቅ አፍሪቃ ስላንዣበበው የረሀብ አደጋ፤ ስለ H.R. 6600 ረቂቅ ሕግ ላይ እንዲሁም የዩክሬን ጦርነት እና የሩስያ ኔቶ ፍጥጫ ላይ የተሰጡ አስተያየቶችን አሰባስበናል። አስተያየቶቹ ከታች በድምፅም በጽሑፍም በዝርዝር ቀርበዋል።