ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
«ጦርነት ከፈታው ወሬ የፈታው» እንደሚባለው ሰዎች በተሳሳተ መረጃ በጥላቻ ለበቀል ሲነሳሱ፣ለአደጋ ሲጋለጡ፣ ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲሸበሩ፣ሲጨነቁና ግራ ሲጋቡ ማየት የተለመደ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የፕሮፓጋንዳው ጦርነት፣ በጦር ግንባር ከሚካሄደው በላይ እየተፋፋመ መሄድ ጦርነቱን ለማስቆም በሚደረጉ የሰላም ጥረቶች ላይም ተጽእኖ እያሳደረ ነው።
በመደበኛ መገናኛ ብዙሃን ላይ እምነት ማጣት ብሎም ሀሳብን በነፃነት ማስተናገድ ያለመቻል ችግር፣አፍራሽ ተፅዕኖው እንዲጨምር ማድረጉን ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ ውይይት ላይ ተነግራል።ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የፖለቲካ ተሳትፎን በማሳደግ፣ ሰዎችን ለበጎ በማሰባሰብ እና በማነሳሳት የማይናቅ አወንታዊ ሚና ቢኖራቸውም አሉታዊ ተፅእኗቸው እየበለጠ ነው።
ግዙፉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴ ፌስቡክ ናይሮቢ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለፈው ሳምንት ክስ ተመስርቶበታል።ድርጅቱ ክስ የተመሠረተበት በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው የርስ በርስ ጦርነት ጥላቻን የሚሰብኩ እና ግጭት የሚያነሳሱ መልዕክቶችን አሰራጭቷል ተብሎ ነው።ከእመልካቾቹ መካከል በፌስ ቡክ የጥላቻ መልዕክት አባቱ የተገደሉበት ተጎጅ ይገኝበታል።
የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች ይፋ በተደረጉበት ስነ ስርዓት፣በጎርጎሮሳዊው 2019 የኖቤል የሰላም የኖቤል ሽልማት ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እንዲሰጥ በተላለፈው ውሳኔ ላይ የተጠየቁት፣ የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ሊቀመንበር ራይስ-አንደርሰን ከዛሬው ተሸላሚዎች ውጭ ስለሌሎች የሰላም ኖቤል ተሸላሚዎች አስተያየት አልሰጥም ብለዋል።