ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ሸርቆለ ወረዳ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ፡፡ በወረዳው በተደረገው አሰሳ 23 በሚደርሱ ጸረ ሰላም በተባሉ ኃይሎች ላይ እርምጃ መወሰዱንና 5ቱን ደግሞ መማረካቸውን የክልሉ ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ወባ፣ አንትራክስ ወይ አባሰንጋ እና ራቢስ በሽታዎች በወረርሽኝ መልክ መቀስቀሱ ተገለፀ። በተለይም የወባ በሽታ በትግራይ በከፍተኛ መጠን እየተሰራጨ ሲሆን በበሽታው የሚለከፉ ሰዎች ቁጥር በየሳምንቱ በ130 በመቶ እያሻቀበ ስለመሆኑ የትግራይ ጤና ቢሮ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ውስጥ ተባብሶ የቀጠለው ግጭትና የዜጎች የኑሮ ውድነት ፈተና እልባት ካላገኘ ወደ ከፋ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚችል የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች ኮከስ አስታወቀ፡፡ ኮከሱ በሳምንቱ መጨረሻ ከተወያዬ በኋላ የዜጎችን ሰቆቃ ለማብቃት አካታች፣ ገለልተኛ እና ግልጽ ብሔራዊ መግባባት ባፋጣኝ እንዲደረግ ጠይቋል፡፡
የፖለቲካ ድርጅቶቹ ተወካዮች ኢትዮጵያውያን ሊስማሙባቸው ባልቻሉባቸው ጉዳይ ላይ ገለልተኛ የዓለማቀፍ ማህበረሰብ ጣልቃ ገብቶ የማደራደር ሚና እንዲጫወት መጋበዝ የአገር ሉዓላዊነትን የሚጥስ አይደለም ብለዋልም፡፡