ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የኢድ አል-ፊጥር በዓል አዲስ አበባ ሲከበር አንድ ፖሊስ «በስሕተት» አፈነዳዉ የተባለ አስለቃሽ ጢስ መዕምናን ማስደንገጡና ማተራመሱ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት 7.2 ሚሊዮን ቤቶች በ10 አመታት ለመገንባት የያዘው ውጥን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ ነበሩ። የፕሬስ ነጻነት ቀን ሲከበር በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች ጉዳይ ተነስቷል።
አርቲስት ቴዲ አፍሮ በወለጋው ጭፍጨፋ ሣልስት ማክሰኞ ዕለት «ናዕት» የተሰኘ ነጠላ ዜማ ለአድማጮች አድርሷል። በዚያኑ ዕለት የጠቅላይ ሚንስትሩ እና ከፍተኛ ባለሥልጣናቱ ስለ ልማት እና «አረንጓዴ ዐሻራ»ን የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸውን በተመለከተም ከኅብረተሰቡ የተሰነዘሩ አስተያየቶችን ቃኝተናል። የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት አተያየቶች።
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጸም ጦርነት፤ የንጹሐን ዜጎች ሞት፣ መፈናቀል እንዲሁም የንብረት ውድመት የየዕለት ዜና ከሆነ ሰነባብቷል። ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱት ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችም በአንድ በኩል መረጃዎችን ማጋራታቸው እንዳለ ሆኖ ሌላ የጦር አውድማ ሆነዋል።
የቆቦ የንፁሃን ግድያ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን መግለጫ፣የቀድሞ የኦነግ ሸኔ የደቡብ ዞን ዋና አዛዥ ሰላማዊ ትግልን ተቀላቀሉ መባል፤የሙሃዘ ጥበባት ዴያቆን ዳንኤል ክብረት ንግግርና የአሜሪካ ውግዘት በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ያነጋገሩ ጉዳዮች ነበሩ።