ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
ፌስቡክ ባለፈዉ ማክሰኞች የጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድን መልዕክት «ሁከትን የሚያባብስ» በሚል ከሠረዘ ወዲሕ ደግሞ መንግሥት የፌስ ቡክ ኩባንያን «የሕወሓት አጋር» በማለት ወቅሷል።
እስክንድር እና ጀዋርን ጨምሮ በእነርሱ መዝገብ የተከሰሱት ከእስር መለቀቅ ለቤተሰቦቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው የፈጠረው ደስታ እና እፎይታ ብዙም ሳይቆይ ትግራይ ውስጥ መንግሥት ሕግ ማስከበር ባለው ጦርነት ተማርከው ለወራት በእስር ቤት የቆዩት 6 ሰዎች መለቀቅ በሕዝብ ዘንድ የፈጠረው ስሜት በማኅበራዊው መገናኛ በተሰራጩ አስተያየቶች ይታያል።
ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴው በዚህ ሳምንትም በበርካታ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። በየጊዜው ለመጠቆም እንደሞከርነው ጽንፍ የያዙ እና ለችግሩ ከመፍትሄ ይልቅ አባባሽ የሆኑትን ወደ ጎን ብለን ትርጉም ያለው ትችት እና ሃሳብ ያዘሉትን መራርጠናል።
ከበዓለ ሲመት እስከ አዲስ መንግሥት ምስረታ፤ ከኢሬቻ በዓል የመንግሥት ተቃውሞ እስከ ተቃዋሚዎች በካቢኔው መግባት ተካቶበታል። የፌስቡክ አጭር መቋረጥ እና የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ መወያየቱም የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት የሳምንቱ ዐበይት መነጋገሪያዎች ነበሩ።