1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ዓርብ፣ ጥቅምት 8 2017

የተደጋገመው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታሪፍ ጭማሪ፤ ባህላዊ የደን አጠባበቅ ስልት በጌዴኦ ፤ የሕወሓት ፖለቲከኞች ለማስታረቅ የተደረገዉ ጥረት አለመሳካቱን

https://p.dw.com/p/4lvWp
Social Media App Symbolbild
ምስል Jonathan Raa/NurPhoto/picture alliance

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የማሕበራዊ መገናኛ ብዙጋን ታዳሚዎች እንደምን ሰነበታችሁ። ዛሬም እንደሁሌው በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከተንሸራሸሩ አበይት ጉዳዮች ዋናዋናዎቹን መርጠን መልሰን ወደእናተው ጀሮ እናደርሳለን።

የተደጋገመው የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ

ከትናንት ወድያ ምሽት በአዲስ አበባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች በድጋሚ የመሬት ንዝረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ እንዳሉት የመሬት ንዝረቱ  ከዚህ ቀደም ከታየው ከፍ ያለ ነበር። ክስተቱ በመዲናዋ አዲስ አበባ ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

በቅርቡም በአፋር ክልል ፈንታሌ ተራራ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ፤ በአዳማ ፣በመተሃራ በአዋሽ አርባ እንዲሁም በመዲናዋ አዲስ አበባ  የተለያዩ አካባቢዎች  የመሬት ንዝረት መታየቱን ነዋሪዎች እና ባለሙያዎች ገልፀው ነበር።

ይህን አስመልክተው ከተሰነዘሩ አስተያየቶች የተወሰኑትን እናስደምጣችሁ።

ማናዊት የሰው ዘር

"አረ ምንድነው የሚሻለን? መሬቱም ኢኮኖሚያችንም እየተንቀጠቀጠ መከራችንን እያየን ነው።" የሚል አጭር አስተያየት አስቀምጧል።

ሐብቴ ባደግ "ሰውን ሰቅለን፣ገድለን፣አፈናቅለን፣ታድያ ምን እንጠብቅ?" በማለት ይጠይቃሉ።

ጆሲ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ "አ.አ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዶርም ሕንፃ ላይ እያለን በትክክል አስተውለናል በተጨማሪም ዛሬ ቀትር ( አስተያየቱ የተጻፈው የመሬት መንቀጥቀጡ ባጋጠመበት ቀን ነው) በኛ አካባቢ በድጋሚ ተከስቷል። " ብሏል።

ሃኖጊን ዊውስ ደግሞ "ስድስት ኪሎ አከባቢ በጣም አስደንጋጭ ነበር ። ልክ ከምሽቱ 5:13 ላይ የተከሰተው ለጥቂት ሰኮንዶች ነበር። ነገር ግን ፎቅ ላይ የነበሩ ነዋሪዎች በድንጋጤ እየሮጡ ሲወጡ ነበር።ተማሪዎች ላይብረሪ ውስጥ ደንግጦ ወንበር ስር ምናምን ወድቀው ሲደበቁ አይተናል ።

የመሬት መንቀጥቀጥ በጣም ያስፈራል ።"

በዚህ ጉዳይ በርካታ አስተያየቶችና ገጠመኞች ተንሸራሽሯል። ዳኒ ያስቀመጡት ሐሳብ ትንሽ ፈገግ ሳያሰኝ አይቀርም "የተንቀጠቀው መሬት አይደለም የመኖር ህልውናችን ነው ወገን " ይላል።

Symbolbild I Facebook und Instagram
ምስል Kirill Kudryavtsev/AFP

በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታሪፍ ጭማሪ

ሌላው በርካታ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት ርእሰ ጉዳይ በአዲስ አበባ ከተማ የመጓጓዣ ታሪፍ ጭማሪ እና የነዋሪው አቤቱታን ይመለከታል።

ከለፈው ሳምንት የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን ተከትሎ  በአዲስ የመጓጓዣ ታፊፍ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ ወትሮም የመጓጓዣ እጥረትና የተጠቃሚዎች መብዛት በሚያጨናንቃት አዲስ አበባ በተለይም በአጭር ርቀት የመጓጓዣ ታሪፍ ላይ እስከ 100 ፐርሰንት የሚደርስ ጭማሪ እንደተደረገ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በዚህ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች የተወሰኑትን እናስደምጣለን።

"ምን ማድረግ ይቻላል የመጣብንን ኑሮ ውድነት እንዴት እንቻለው?" የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት ያስቀመጡት ጥላዬ ከበደና ቸው።

ራስ አምነህ "ገቢ ና ወጪዬ ሰማይና ምድር ሆነብኝ! መሮኛል የት ሆጄ አቤት ልበል?" የሚል አስተያየት ከ7 የሐዘን መግለጫ የኢሞጂ ምስል ጋር አስቀምጧል።

"መንግስት የዋጋ ማሻሻያ እያለ እራሱ የሚያስተዳድራቸውን ድርጅቶች የማይቀመሱ፣ የማይነኩ እያደረጋቸው ነው።ለምሳሌ ቴሌን፣ ፖስፖርትና አየር መንገድ ማየት ብቻ በቂ ነው። መንግስት በቻለው አቅም ከራሱ ጥቅም ይልቅ ለዜጎች ጥቅም ቢታገል የተሻለ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተቻችሎ መኖር ይችልበታል። ስለዚህ ከትንሽ እስከ ትልቅ ያሉ ቦታዎችን በዋጋ ንረት መነቃነቅ መንግሰትን ከባድ ቸግር ላይ ይጥላል። መንግስት ለዜጎች ሲጨነቅ ዜጎችም ለመንግስታቸው ታማኝ ይሆናሉ።" የሚል አስተያየት ያስቀመጡት ደግሞ መሱድ አሊ ናቸው።

አትንኩት ገላጋይ "መንግስት ኮሪደር ልማት እያለ ህዝብ በኑሮውድነት አጨናኑቆታል፤ ለርሃብ ተጋልጧል። ሰርቶ ለመብላት ተቸግሯል።  በዚህ የንሮውድነት በዚያ ጦርነት ተንቀሳቅሰን ሰርተን እንዳንበላ ትራንስፖርት ዋጋ በእጥፍ አርጎታል" የሚል አስተያየት ፅፏል።

ተስፋዬ ዘገዬ "ለማን ነዉ አቤት የምትለው መንግስት ሁሉንም ያውቃል" የሚል አጭር አስተያየት ሲያስቀምጥ ጃም የተባሉ ደግሞ "በብርታት በጥንካሬ አስቸጋሪዉን ግዜ እንሻገረዋለን።" ብሏል።

Logo | US-amerikanischer Internetkonzern | Meta
ምስል Annegret Hilse/REUTERS

ባህላዊ የደን አጠባበቅ ስልት በጌዴኦ 

የደን መራቆት የበርካታ ሃገራት ችግር መሆኑ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በገሀድ እየታየ መጥቷል። በደን መራቆት ለድርቅና ረሀብ ከሚጋለጡት ሃገራት አንዷ ደግሞ ኢትዮጵያ ናት። የደን ሀብቷ በየዓመቱ በከፍተኛ ደረጃ እየተመናመነ በሄደባት ኢትዮጵያ የጌዴኦ ማኅበረሰብ በተፈጥሮ አረንጓዴ ምንጣፍ ላይ ይኖራል። ይህን የጌድኦ ሕዝብ ባሕላዊ የደን ልማት በተመለከተ ከተነሱ ሐሳቦች የተወሰኑትን እናስደምጣችሁ።

"እኛ ጌዴኦዎች ለደን ያለንበት ቦታ ከፈተኛ ነው አንድ ዛፍ ስንቆርጥ ከስሩ ተተኪ ዛፍ ተክለን ነው።" የሚል ሐሳብ ያሰፈሩት ሐብታሙ ንጉሴ ናቸው። አቤል ደግፌም "ለጌደኦ ህዚብ ደንን ጥላ ብቻ ሳይሆን ህይወት ጭምር ነው አንድ ዛፍ ያለ አግባብ አይቆርጥም!" ብሏል።

ተክላይ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው "የዓለም ሙቀት ከጊዜ ወደጊዜ በመጨመሩ ምክንያት ምድራችን ለሰው ልጆች የማትመች እየሆነች ትገኛለች። ብዙ ያልተጠበቀ የተፈጥሮ አደጋ ክስተቶች በሰው ልጆች ላይ እየደረሰ መሆኑ የተለመደ ሆኗል። ለዓለም ሙቀት መጨመር ዋነኛው መንስኤ ሰዎች የሚያደርጉት ነገር መሆኑን ብዙ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።

ይህም ይዞ የሚመጣው መዘዞች አንዱ መጥፎ የአየር ሁኔታዎች እየጨመረ መምጣቱ ሲሆን ይህን ተከትሎ እጅግ ሞቃታማ ወቅቶች፣ድርቅና ከባድ ዝናብ በምድር ላይ ይሆናል።ከነዚህ ተለዋዋጭ የአየር ንብረት ሁኔታዎች የተነሳ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣የመሬት መንቀጥቀጥ፣የወንዞች መሙላት ፣የባህር ጠለል ከፍታ መጨመር፣የበረዶ ግግር መቅለጥ፣የሰደድ እሳት፣ የአየር ወለድ በሽታ (ወረርሽኝ) በደረቅ አየር ተባዝቶ የመከሰት እና የተለያየ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና አዕምሯዊ ቀውስ ሲፈጠር ወደ ማያባራ አለመግባባትም ይመራናል።

ሆኖም ሀገራችን የአየር ንብረት ለውጥ ሚዛኑን ጠብቆ እንዲሄድ እያደረገች ያለው አስተዋጽኦ አበረታች መሆኑን ማሳያው በአንድ ጀምበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች እየተተከለ መሆኑ ነው።ከተተከለው ምን ያህል እንደፀደቀ ሪፖርት መስማት ናፍቆኛል።

ለጌዴኦ ሕዝብ የላቀ ምስጋና አለኝ።"

እምነት ክፍሌ "ሚስጥሩ ጌድኦ ባቦ የሚባል ሥርዓት አለው ።ባቦ ማለት አንድ ዛፍ በተቆረጠበት ምትክ 2 እና ከዛ በላይ ዛፎች መትከል ማለት ነው።" በማለት የጌድኦዎች የደን ልማትን አድንቀዋል።

"የቀደመ፣የመጠቀ በአርቆ አሳቢነት ለረዥም ዘመናት ማህበረሰባችን የኖረበት ድንቅ የደን አጠባበቅ ባህል በሙቀት መጨመር ለምትሰቃዬው ዓለም ሁሉ መማርያም ማስተማርያም የሆነ ድንቅ የጌዴኦ ምድር ! ይህንኑ ተሞክሮ ሌላ ማህበረሰብና ዓለም ሃገራት መውሰድ አለበት።" ያሉት ደግሞ ደጀኔ ዳካ ናቸው።

Frankreich Nantes | Logo des sozialen Netzwerks TikTok
ምስል Loic Venance/AFP/Getty Images

የሕወሓት ፖለቲከኞች ለማስታረቅ የተደረገዉ ጥረት አለመሳካቱን

የተከፋፈሉትን የሕወሓት ፖለቲከኞች ለማስታረቅ የተደረገዉ ጥረት አለመሳካቱን የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ትኩረት ከሳቡ ርእሰ ጉዳዮች አንዱ ነበረ።

"ፖለቲካው እሱን ካልጠቀመው፣ ካልተመቸው ህዝቡን ገደል የሚጨምር ፖለቲከኛ ያለው አፍሪካ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ይቀራል?" የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት ያሰፈሩት ንጋቱ ናቸው።

"እኔ ትግራዋይ አደለሁም ኢትዮጵያዊ ነኝ። ትግራይም ኢቲዮጵያ ነች" በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት ደግሞ የእናት ሐገር አጥርና ማገር በሚል መጠሪያ የጻፉ አስተያየት ሰጪ ናቸው። እሳቸው ስም በመጥቀስ የህወሓት መሪዎችን ከወቀሱ በኋላ  "የናንተ የፓለቲካ የበላይነት ይቅርባቹ፤ ለትግራይ እናቶች ስትሉ ልዩነታችሁን አጥብባችሁ በመቻቻል ሰላም ፍጠሩ አደይ አረፍ ትበል፤ ይስማል ሀሎ!" ብለዋል። ውድ ተሳታፊያችን ስም በመጥቀስ ያስቀመጡት ሐሳብ ባለመውሰዳችን ቅር እንደማይሰኙ ተስፋ እናደርጋለን።

መኮነን ገብረጻዲቅ ደግሞ በዘገባው በስጨት ያሉ ይመስላል "ሁሉም ነገር የምታወሩት እናንተ ናችሁ። ሊታረቁነው ኣላችሁ እሺ ኣልን፤ ኣልተሳካም ኣላችሁ እሺ እንላለን። እነሱ ግን ምንም ያሉት ነገር የለም። ባዕልኺ መውፅኢት ደርፊ በዕልኺ መጥፍኢት ደርፊ የሚባል ነገረ ኣለ በትግርኛ" አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው እንደማለት ነው።

 ሰገነት ባደግ " ነገር ማይሰለቻቸው ጦርነት ማይሰለቻቸው ሞት ማይሰለቻቸው" የሚል አስተያየት አስፍራለች።

 ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 

ሽዋዬ ለገሰ