የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት | የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት | DW | 05.02.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

የዛሬው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ዝግጅት በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ያነጋገሩ ጉዳዮች ተካተውበታል። በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ቀናት ብቻ አምስት የእሳት አደጋ ማጋጠሙ አነጋግሯል። የድሬዳዋ እና የአዲስ አበባ ምርጫ ቀን ጉዳይም ተነስቷል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:35

በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ቀናት ብቻ አምስት የእሳት አደጋ

የዛሬው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ዝግጅትበአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ቀናት ብቻ አምስት የእሳት አደጋ ማጋጠሙ አነጋግሯል። የድሬዳዋ እና የአዲስ አበባ ምርጫ ቀን ጉዳይም ተነስቷል። ቤተማርያም አለሙ «የአዲስ አበባ ህዝብ በምርጫው የመጀመሪያ ቀን እንዳይመርጥ መደርጉን እጅግ እሳዛኝ ነው!»ሲሉ፤ መርሻ ተረፈ በበኩላቸው «የአዲስአበባን ህዝብ ድምፅ የማኮስስ እና በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል ላይ የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌትነቱን ለመቀማት ሆን ተብሎ የተሰራ ይመስላል።» ብለዋል። ሀፊዝ ሃሚድ ደግሞ «ይህ የምርጫ ሰሌዳ ሁለት ጊዜ እንዲመረርጡ ለሚፈለጉ ሰዎች ታሥቦ ነው። ለሚል ግምት አጋልጦኛል።»ብለዋል።ቢንያም ዳባ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ «በመጀመሪያ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ያወጡት መግለጫም ይሁን የተሳትፎ መድረኩ ምርጫ ቦርዱ በኢትዮጵያ ታሪክ የተሻለ ሰው ያገኘበትና አንድ እርምጃና ድሞክራሲን ያየንበት ሆኖ አግኝቸዋለሁ።»ነገር ግን የድሬዳዋ እና የአዲስ አበባ ምርጫ ለምን በተለየ ቀን ማካሄድ እንዳስፈለገ በጭራሽ አልገባኝም»ብለዋል። 
ኪራ ሀይሌ በበኩላቸው «ለምንድነው የአ.አ ከተማ አስተዳደር ምርጫ ከሀገር አቀፍ ምረጫው እንዲዘገይ የተደረገው? የአዲስ አበባን መታወቂያ በህገወጥ መንገድ ወስደዋል ለተባሉ የክልል ነዋሪዎች በድጋሜ እንዲመርጡ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ይታሰብበት።ብለዋል። 
«የምርጫው ቀን መቼም ይሁን መች ዋናው ምርጫው ፍትሃዊ ከሆነ ችግር የለውም።ይህንን ነው ለምርጫ ቦርድ ማሳሰብ ያለብን።»ያሉት ደግሞ ሀረጓ አዲስ ናቸው። 

ሌላው በዚህ ሳምንት የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ያነጋገረው ጉዳይ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአዲስ አበባ ከተማ በሁለት ቀናት ብቻ አምስት የእሳት አደጋ ማጋጠሙ ነበር።በከተማዋ ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በጉለሌ በቂርቆስ ፣በኮልፌና በቦሌ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ አምስት ቦታዎች የጉለሌ የእፅዋት ማዕከልን ጨምሮ በመኖሪያ ቤት፣በህንፃና የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።በደረሰው እሳት አደጋም የዕፅዋት ማዕከሉ ሁለት ሄክታር መሬትና በርካታ ንብረት መውደሙ ተገልጿል። 
ሶሎሞን ወልደማርያም «እውነቱ በክልልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ በየአቅጣጫው፣በገበያ.ሥፍራ፣ በሀገርና በህዝብ ንብረት የሚለከሰው እሳት ምክንያቱ በደንብ ቢጣራ መልካም ነው።ወይስ ድሃና ለማኝ ለማብዛት የሚደረግ ነው።»ሲሉ፤ 
ብርሃኑ አባተ ደግሞ «የዚህ የእሳት ነገር በሚገባ ሊጣራና ክትትል ሊደረግበት የሚገባ ይመስለኛል ተደጋገሟል። የጤና አይመስልም ። ሀላችንም ከተማችንን ነቅተን የምንጠብቅበት ጌዜ ነው።»ብለዋል። 
ጀማል ኢብሮ በበኩላቸው « በቦታው ከወትሮ በተለየ ሁኔታ እየተከሰተ ያለው የእሳት አደጋ ድንገተኛ ነው ብሎ ማሰብ እራስን ማሞኘት ነው። የሆነ ተልእኮ ያለው አካል ይህን እያደረገ ያለ ይመስለኛል።» የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ማርታ ፈይሳ ደግሞ «ኑሮውም ፖለቲካውም እሳት ሆኖብናል ሌላ እሳት አንፈልግም።« የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። 
ክሪስ ክሪስ በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረው አስተያየት ደግሞ «እኔ ግን ቦታው ለዶሞግራፊ ቅየራ ተፈልጎ ነው የሚመስለኝ »ሲሉ፤ 
መሰሉ አበበ ደግሞ «በሐገራችን ኢትዮጵያ የሳት አደጋና የትራፊክ አደጋ እየጨመረ ነው። በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት ቢሰራ ጥሩ ነው።እኛም የሴራ ትንተናውን ትተን ብንጠነቀቅ ይሻላል።» የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።» 
እሌኒ ሀጎስ የተባሉ አስተያየት ሰጪ «ረሃብና ስደትን እንደማጥፋት ሰውንና ንብረትን ማጥፋት ተገቢ አይደለም።» ብለዋል ።»በቀለ ሽኩር በበኩላቸው «የማቃጠል ፖለቲካ የት ያደርሳል» ሲሉ፤ ተክሌ ክፍሌ የተባሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ «የእጅ ሥራ ያለበት ይመስለኛል። በተለይ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ ኤምባሲ ለዜጎቹ ባወጣው የጉዞ ክልከላ ላይ የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል አንዱ መሆኑን ሳስብ።ነገር ግን የሀገር ንብረት በማቃጠል የሚገኝ ትርፍ የለም። ቃጠሎው ከቀጠለ ተረኛ ተቃጣይ ይኖራል እንጂ ስልጣን አያስገኝም።»ብለዋል። 
ጀስቲስ ፎር ኦል የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ደግሞ 
«ወይ አዲስ አበባ፣ ወይ አራዳ ሆይ፤ 
እሳት የሚያጠፋ ዘመድ አጣሽ ወይ።»በማለት አስተያየታቸውን በግጥም አጋርተዋል። 
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ 110 የእሳት አደጋዎች መድረሳቸውን አስታወቆ፤ አብዛኛዎቹ ፡በጥንቃቄ ጉድለት የደረሱ አደጋዎች ናቸው ማለቱን ያለፈው ማክሰኞ በነዚሁ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተመልክተናል። 

ፀሐይ ጫኔ 

Audios and videos on the topic