የማኅበራዊ መገናኛዎች እና ኔትወርክ ችግር | ኢትዮጵያ | DW | 14.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የማኅበራዊ መገናኛዎች እና ኔትወርክ ችግር

ካለፈዉ ቅዳሜ ዕለት አንስቶ ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደፌስቡክ ትዊተር፣ ኢንስታግራም፤ እና ቫይበርን የመሳሰሉ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መዘጋታቸዉ በይፋ ተንግሯል። የመንግስት ቃል አቀባይ በወቅቱ እንዳስታወቁት እነዚህ መገናኛ ዘዴዎች የሚዘጉት እስከትናንት ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17

ማኅበራዊ መገናኛዎች

ምንም እንኳን አንዳንዶች አቋራጭ መንገዶችን በመጠቀም የተባሉት መገናኛ ዘዴዎች መክፈት ቢችሉም ባብዛኛዉ ግን ተመልሰዉ እንደወትሮዉ ሥራ አለመጀመራቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዛሬዉ ዕለት ደግሞ እኛም ከዚህ ከዶቼ ቬለ ለተለያዩ የሥራ ጉዳዮዎች ወደኢትዮጵያ ያደረግናቸዉ የሥልክ ጥሪዎች መግባት አልቻሉም። አልፎ አልፎ አንዳንዶ ስልኮች ጠርተዉ ማነጋገር ብንችልም በአብዛኛዉ ኔትወርኩ ሥራ በዝቶበታል፤ ወይም ዘ ኔትወርክ ኢዝቢዚ ናዉ የሚል መልዕክት ነዉ ሲተላለፍ ያስተዋልነዉ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ያገኘሁትን የአዲስ አበባ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን ስለሁኔታዉ አነጋግሬዉ ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic