የማራታኔ ስደተኖች ይዞታ | ኢትዮጵያ | DW | 07.10.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የማራታኔ ስደተኖች ይዞታ

ሰሜን ምስራቅ ሞዛምቢክ የሚገኘው ማራታኔ ደቡባዊ አፍሪቃ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የስደተኞች መጠለያዎች አንዱ ነው ። በአሁኑ ጊዜ በዚህ ጣቢያ ከአምስት ሺህ የሚበልጡ ስደተኞች ይገኛሉ ።

default

በሰሜን ሞዛምቢክ፣ ናምፑላ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው -ማራታኔ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፣

ከመካከላቸው ብዙዎቹ ከዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ነው የመጡት ። ማራታኔ ከሚኖሩት ስደተኞች አብዛናዎቹ ከታላላቆቹ ኃይቆች ሀገራት ቢሆኑም እንደ ሶማሊያ እና ኤርትራ ከመሳሰሉ የአፍሪቃ ቀንድ አገራት የመጡም ይገኙበታል ። በቅርቡ ወደ ማራታኔ የስደተኞች መጠለያ የተጓዘው የዶይቼቬለ ባልደረባ António Cascais በስፍራው የስደተኞች ይዞታ ምን እንደሚመስል ዘግቧል ። ሂሩት መለሰ አቀናብራዋለች ።

ሂሩት መለሰ፣ ነጋሽ መሐመድ፣

ተክሌ የኋላ፣