የማሊ ጦር ሠራዊት ሥልጠና | አፍሪቃ | DW | 06.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ጦር ሠራዊት ሥልጠና

የአውሮጳ ህብረት ባለፈው ማክሰኞ፡ እአአ ሚያዝያ ሁለት፡ 2013 ዓም የማሊን መንግሥት ጦር የማሠልጠን ተልዕኮውን በይፋ መጀመሩን በብራስልስ የሚገኙት የአውሮጳ ህብረት ቃል አቀባይ ማይክልማን ገልጸዋል።

እንድርሳቸው ገለጻ፣ በወቅቱ የተለያዩ የማሊ ጦር ኃይላት ቡድኖች የሚያሠለጥኑ ወደ ሁለት መቶ ፡ ሁለት መቶ ሀምሣ አሠልጣኞች በሀገሪቱ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም ደጋፊ እና ከለላ ሰጪ ኃይላትም አሉ። ሁለት መቶ የህብረቱ አሠልጣኞች የማሊ ሠራዊት አስፈላጊው ጥንካሬ እና ስልት እንዲኖረው ያስችላል የሚባለው ሥልጠና የሚሰጡት ከማሊ ዋና ከተማ ባማኮ 60 ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው ኩሊኮሮ  በተባለችው ከተማ  ነው።

አርያም ተክሌ

መሥፍን መኮንን

Audios and videos on the topic