የማሊ ጦርነትና የፈረንሳይ ዕቅድ | አፍሪቃ | DW | 07.02.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ጦርነትና የፈረንሳይ ዕቅድ

ፈረንሳዮች ለዚሕ ድል በመብቃታቸዉ ከምዕራብ፥ ተሻራኪዎቻቸዉ፥ ከአፍሪቃ ወዳጆቻቸዉም ድጋፍ እየጎረፈላቸዉ ነዉ።ለማሊ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለቲማን ሁበርት ኮዉልባሊ ደግሞ የቀድሞ የሐገራቸዉ ቅኝ ገዢ የፈረንሳይ ዉለታ ነብስ ከማዳን የሚቆጠር ነዉ።

GettyImages 160777278 Guinea troops parade on February 5, 2013 before their departure for Mali at the military base at Kindia. AFP PHOTO/CELLOU BINANI (Photo credit should read CELLOU BINANI/AFP/Getty Images)

የጊኒ (ኤኮዋስ) ጦር


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የማሊን ሠላም የሚያስከር ሠራዊት እንዲያዘምት ፈረንሳይ ያቀረበችዉን ጥያቄ ተቀብለዉ።ትናንት በዝግ የተነጋገሩት የምክር ቤቱ አባላት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ለማዝመት መስማማታቸዉን አስታዉቀዋል።የቀድሞዋ የማሊ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ ሰሜናዊ ማሊን ይቆጣጠሩ የነበሩትን አማፂያንን እንዲወጋ ያዘመተችዉ ጦሯን ከማሊ ለማስወጣት አቅዳለች።የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ECOWAS) እና የቻድ ጦር ግን ፈረንሳይ ጦር ከወጣም በሕዋላ እዚያዉ ማሊ ይቆያል።የማሊን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ነጋሽ መሐመድ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለ።


የፈረንሳይ የጦርና የፖለቲካ መሪዎች በየፊናቸዉ እንዳሉት በሐገራቸዉ የቀድሞ ቅኝ ተገዢ ማሊ ላይ ማድረግ-የፈለጉትን በፈለጉበት ወቅት ማድረጉ ከሞላ ጎደል ተሳክቶላቸዋል።አሸባሪ፥ ጂሐዲስት፥ አክራሪ እና ሌላም የሚባሉትን አማፂያንን እንዲወጋ ያዘመቱት ጦር ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ጠላቶቹን ሙሉ በሙሉ ደምስሶ፥ ከራሷ ከፈረንሳይ ግዛት የሚሰፋዉን ሰሜናዊ ማሊን ተቆጣጥሯል።ባዮች ናቸዉ-ባለሥልጣናቱ።

ፈረንሳዮች ለዚሕ ድል በመብቃታቸዉ ከምዕራብ፥ ተሻራኪዎቻቸዉ፥ ከአፍሪቃ ወዳጆቻቸዉም ድጋፍ እየጎረፈላቸዉ ነዉ።ለማሊ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለቲማን ሁበርት ኮዉልባሊ ደግሞ የቀድሞ የሐገራቸዉ ቅኝ ገዢ የፈረንሳይ ዉለታ ነብስ ከማዳን የሚቆጠር ነዉ።

«የፈረንሳይ የጦርጄቶች ባይደግፉን ኖሮ ሪፐብሊካዊት (ሐገራችን) ዛሬ አትኖርም ነበር»

GettyImages 160772088 A man searches on February 5, 2013 in the ruins of a building destroyed by French air strikes in Douentza.The town was retaken by French and Malian troops in January. AFP PHOTO / PASCAL GUYOT (Photo credit should read PASCAL GUYOT/AFP/Getty Images)

የጦርነቱ ድቀትየመብት ተሟጋቾች ግን በፈረንሳይ ጦር የሚመራዉ የማሊ መንግሥት ጦር በመቶ የሚቆጠሩ የሰሜናዊ ማሊ ነዋሪዎችን ማሰር፥ መግረፉ በጅምላ መረሸኑን በተደጋጋሚ ዘግበዋል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ደግሞ ጦርነቱ ያፈናቀላዉ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ የሰሜን ማሊ ሕዝብ በረሐብ እየነፈረ ነዉ።

የማሊ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በፈረንሳይ ጦር ድብደባ «ዳነች» ያሏት ሐገራዉቸዉ የተገደለ፥ የሚሰቃይ፥ የሚራብ ሕዝቧም ሐገር-መሆን አለመሆኗ በርግጥ አጠያያቂ ነዉ።ማሊን በዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ ቋንቋ «ያዳናዉ» የፈረንሳይ ጦር በቅርቡ በተቆጣጠራት ጋኦ ከተማ አማፂያኑ በፈረንሳይና በማሊ መንግሥት ወታደሮች ላይ ትናንት መጠላቸዉ አላነጋገረም።የፈረንሳዩ መከላከያ ሚንስትር ዤ ኢቭ ለ ዳርዮ እንዳሉት አደጋ ጣዮቹ የጂሐዲስቶቹ ጥቂት ቅሪቶች እንጂ የሐያል ሐገራቸዉን ሐያል ጦር የሚያሰጉ፥ ታላቅ-ድሉን የሚቀለብሱም አይደሉም።

ፕሬዝዳት ፍሯንሷ ኦላንድ በበኩላቸዉ አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ወይም በመጥፋታቸዉ ለማሊ ወቅቱ የድርድርና የእረቀ-ሠላም ነዉ-ይላሉ።

«የማሊ የግዛት ሉዓላዊነት የተከበረበት ያሁኑ ወቅት የድርድርና የእርቅ ጊዜ መቃረቡን ጠቋሚ ነዉ።»
ሙስሊም አሸባሪ፥ ጂሐዲስት ፅንፈኛ የሚባሉት አማፂያን «ጠፍተዋል» ይላሉ-የማሊ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነትም ተመልሷል።ማን ከማን ጋር እንደሚደራደር፥ ወይም እንደሚታረቅ ግን ግልፅ አይደለም።ግልፅ የሆነዉ ፈረንሳይ ለማሊዉ ዘመቻ ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ከሰባ ሚሊዮን ዩሮ በላይ ማዉጣትዋ ነዉ።

ጀርመንና ብሪታንያን የመሳሰሉ የአዉሮጳ ሐገራትና የዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ ባይታከልበት ደግሞ ወጪዉ ከእጥፍ ይበልጥ ነበር።ፈረንሳይ እስካሁን ካወጣችዉ በላይ ተጨማሪ ገንዘብ ማዉጣት፥ አትፈልግም።ወይም አትችልም።ምናልባትም ጦርነቱ መልኩን ቀይሮ የደፈጣ ዉጊያ መልክና ባሕሪ ይዞ ከተራዘመ ፈረንሳዮች ደማቸዉን ለማሊ በረሐ መገበር አይፈልጉም።

Mali's Foreign Minister Tieman Hubert Coulibaly attends a meeting at the European Union Council in Brussels to discuss the crisis in Mali February 5, 2013. Governments and international organisations meet on Tuesday to find ways to reinforce military gains against Islamist rebels in northern Mali by supporting democracy, economic development and human rights in one of the world's poorest countries. REUTERS/Francois Lenoir (BELGIUM - Tags: POLITICS)

የማሊ ዉጉሚ

የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት እንዲያዘምት ፓሪሶች የጠየቁትም ለዚሕ ነዉ።የፈረንሳዩ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሎራ ፋቢዮስ እንዳሉት ድርጅቱ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት እንዲሠፍር ከወሰነ፥ «አሁን ያለዉ መዋቅር» እንዳለ ይቀጥላል።ይሕ ማለት እስካሁን የዘመተዉ የቻድና የኤኮዋስ ጦር ሠማያዊ መለዮ-ለብሶ፥ በአዉሮጶች ከሚሠለጥነዉ የማሊ መንግሥት ጦር ጋር በመሆን፥ የፈረንሳዩ መከላከያ ሚንስትር ዳርዮ «ቅሪቶች» ካሏቸዉ አማፂያን ጋር ይጋፈጣል ማለት ነዉ።

የባማኮዉን ወጣት ያስጨነቀዉ ግን የሐገሩ እግር ኳስ ቡድን መሸነፍ ነዉ።«ቡድናችን ለአፍሪቃ ዋንጫ ለግማሽ ፍፃሜ አልፎ-ቢሆን ኖሮ» አለ ዲያካሪ ዲያ «ላጭር ጊዜም ቢሆን ከጦርነት ወሬ ተንፈስ እንል ነበር።» አከለ የሃያ-አንድ ዓመቱ ወጣት።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic