የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ | አፍሪቃ | DW | 11.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ

በማሊ የሽብር ጥቃት በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ተነገረ። የሀገሪቱ መንግሥት እንዳስታወቀው ከሆነ ለጥበቃ የተሰማራ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ፈንጂ ረግጦ በመንጎዱ ቢያንስ ሦስት ወታደሮች ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው 4የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኖችን ጨምሮ 13 ሰዎች ሆቴል ውስጥ በተከሰተው የአጋች ታጋች ግብግብ ከተገደሉ ከ4 ቀናት በኋላ መኾኑ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:18
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:18 ደቂቃ

የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእረፍት ተዘግቶ አብዛኞቹ አባላቱ ወደየመኖሪያ ቀዬያቸው አቅንተዋል። ከሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ለመጡ አብዛኞቹ የምክር ቤት አባላት ግን በአሁኑ ወቅት ወደ መጡበት መመለስ የሚታሰብ አይደለም። ግድያ እና የፈንጂ ጥቃት በማሊ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ፊሊፕ ዛንድነር/ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic