የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ | አፍሪቃ | DW | 27.07.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ

ማሊን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት እቅድ አውጤቻለሁ የሚለው የማሊ የሽግግር መንግስት ከሃገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃወሞ ገጥሞታል ። መንግሥት የአመራር ብቃት ይጎድለዋል ሲሉ የተቹት እነዚሁ ፓርቲዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን እንዲወርዱ ትናንት ጠይቀዋል ።

ማሊን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት እቅድ አውጤቻለሁ የሚለው የማሊ የሽግግር መንግስት ከሃገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተቃወሞ ገጥሞታል ። መንግሥት የአመራር ብቃት ይጎድለዋል ሲሉ የተቹት እነዚሁ ፓርቲዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን እንዲወርዱ ትናንት ጠይቀዋል ። በሌላ በኩል ፓሪስ ፈረንሳይ ሲታከሙ የቆዩት የማሊ የሽግግር መንግሥት ፕሬዝዳንት ዲዮንኩንዳ ትራኦሬ ዛሬ ማምሻውን ወደሃገራቸው ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሞዲቦ ዲያራ የሚመራው የማሊ የሽግግር መንግሥት ከተመሰረተ ገና 3 ወሩ ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዲያራ እስከ መጪው ማክሰኞ ማለትም ሐምሌ 24 ፣ 2004 ዓም ድረስ ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲመሰርቱ የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ማህበረሰብ በምህፃሩ ኤኮዋስ አዟል ። የሚመሰረተው መንግሥትም ከ 4 ወራት በፊት ሰሜናዊ ማሊን ከተቆጣጠረው አክራሪ ሙስሊም ኃይል ጋር አንድ አይነት ስምምነት ላይ እንዲደርስ የአካባቢው ሸምጋይ ሃገራት ጠይቀዋል ። ይሁንና ይህ ሃላፊነት የተሰጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዲያራ ሥልጣን እንዲለቁ የማሊ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበራት ጠይቀዋል ።

Malian nationals arrive from the northern cities of Gao and Mopti at the Bamako bus station after two days of travel on April 7, 2012. Coup leaders in Mali have agreed to stand down and allow a transition to civil rule as part of a deal struck with the West African regional bloc, Ecowas. The deal, signed by coup leader Captain Amadou Sanogo, will see an end to sanctions against Mali and power handed to the head of the national assembly. But no timetable has been set for the handover, and Tuareg rebels in the north have declared independence for the territory they call Azawad. Photo by Julien Tack/ABACAPRESS.COM # 315986_011

Mali Flüchtlinge

ከነዚህም አንዱ በእንግሊዘኛው ምህፃር FDR በመባልየሚጠራውየተባበሩት የሪፐብሊኩ ና የዲሞክራሲ መከላከያ ግንባሩ ነው ግንባሩ ባወጣው መግለጫ በዲያራ የሚመራው የማሊ የሽግግር መንግሥት የአመራርብቃት የለውም ሃገሪቱም የሽግግሩ መንግሥት ከተቋቋመ አንስቶ የኃሊት እየሄደች ነው በማለት ጠቅላይሚኒስትሩ ከሥልጣን እንዲወርዱ ጠይቋል። ሆኖም የማሊን ሁኔታ በቅርበትየሚከታተሉ ወገኖች ይህ ጥያቄ የተነሳበትወቅትተገቢአ ይደለምይላሉ ። ከነዚህም አንዱ የ Inter-African Union of Human Rights በምህፃሩ IUHR ወይም አፍሪቃ አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ፕሬዝዳንት ባሂማ ኮኔ ናቸው ።

« ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሽግግሩ ወቅት ይችን ሃገር ሊመሩ የሚችሉ ሰዎች በአጠገባቸው ቢኖሩ ኖሮ በዚህ ቀውጢ ሰዓት መንግሥት ሥልጣኑን እንዲለቅ የተጠየቀበትን ሁኔታ ማሟላቱ ባልገደደም ነበር ። በሰሜን የሃገሪቱ ክፍል የደረሰውን ቀውስ ማስወገድ የሚቻልበትን ሠላማዊ መፍትሄ ለማስገኘትን ምርጫን ለማደራጀትም በተቻለ ነበር ። ይሄን የሚያደርግ ቡድን ነበረ የሚያስፈልገን ። »

Malian nationals arrive from the northern cities of Gao and Mopti at the Bamako bus station after two days of travel on April 7, 2012. Coup leaders in Mali have agreed to stand down and allow a transition to civil rule as part of a deal struck with the West African regional bloc, Ecowas. The deal, signed by coup leader Captain Amadou Sanogo, will see an end to sanctions against Mali and power handed to the head of the national assembly. But no timetable has been set for the handover, and Tuareg rebels in the north have declared independence for the territory they call Azawad. Photo by Julien Tack/ABACAPRESS.COM # 315986_011

Mali Flüchtlinge

ኮኔ የተቃወሙትን ሃሳብ ያቀረበው FDR ዲያራን የሚተቸው በአክራሪ ሙስሊሞች የተያዘውን ሰሜን ማሊን በጦርነትም ይሁን በድርድር ለማስለቀቅ አንዳችም ስልት አልቀየሱም ሲል ነው ። ግንባሩ ማሊን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ከገባችበት ቀውስ ያወጣል ሲል የሽግግር መንግሥቱ የቀየሰውን የሰላም እቅድም ራዕይ አልባ ነው ያለው እጅግ አንገብጋቢና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ ብሔራዊ ጉዳዮችን እምብዛም አላካተተም ብሏል ግንባሩ ። በነዚህ ምክንያቶችም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን ይውረዱ እያለ ነው ። ይሁንና የአፍሪቃ አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ፕሬዝዳንት ባሂማ ኮኔ በዚህ አይስማሙም በርሳቸው አስተያየት የሽግግሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን መልቀቅ ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም ። ይህን ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖችም በቅድሚያ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል ።

«የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከሥልጣን ቢያነሱ እርምጃው ሃገሪቱን ወደ ባሰ ቀውስ ውስጥ ነው የሚከታት ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ሁሉ በመጀመሪያ የቤት ሥራቸውን መሥራት ይኖርባቸዋል ። ሃገሪቱም በስተመጨረሻ ከገባችበት ማጥ ማውጣት መቻል ይኖርባቸዋል »

በርግጥም የሽግግሩ መንግሥት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አክራሪ ሙስሊሞች በሰሜን ማሊ ይዞታቸውን እያጠናከሩ ነው የሄዱት ። ምትክ የሌላቸውንም የዓለም ቅርሶችም አውድመዋል ። በሰሜን ማሊ መያዝ ሰበብ 400 ሺህ ማሊዎች ተፈናቅለዋል ። የማሊ የሽግግር መንግሥት ዋነኛ ሃላፊነት ለሰሜን ማሊ ቀውስ መፍትሄ መሻት የነበረ ቢሆንም በዚህ ረገድ አንዳች የፈየደው ነገር የለም ። የሽግግሩ መንግሥት ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲመሰርት ሸምጋዩ የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሃብት ማህበረሰብ አዟል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲወርዱ ስለ ለተነሳው ጥያቄ የሸምጋዮቹ አንድ ምንጭ በሰጡት መልስ ይህ በማሊዎች ነው የሚወሰነው ብለዋል ። የማሊው የሽግግር ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው የተባበሩትየሪፐብሊኩናየዲሞክራሲመከላከያግንባርካካተታቸው ፓርቲዎች ውስጥ የሽግግሩ መንግሥት ፕሬዝዳንት የዲዮንኩንዳ ትራኦሬ የማሊ ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፓርቲ ይገኝበታል ። በምርጫ ሥልጣን የያዙትን የቀድሞ የማሊ ፕሬዝዳንት አማዱ ቱማኒ ቱሬን በመጋቢት ወር በመፈንቅለ መንግሥት ክሥልጣን ያስወገዱት ዲያኮንዳ ትራኦሬ ከሁለት ወራት የፓሪስ ፈረንሳይ ህክምናቸው በኋላ ዛሪ ወደ ሃገራቸው ይመለሳሉ ። ቱሬ ባለፈው ግንቦት የሽግግሩ መንግሥት በይፋ ስራውን በሚጀምርበት ዋዜማ ላይ ነበር በቢሮአቸው ውስጥ በተነሳ አመፅ ከተጎዱ በኋላ ፈረንሳይ ለህክምና የሄዱት ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 27.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15f6b
 • ቀን 27.07.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/15f6b