የማሊ ቀውስ እና የአልጀሪያ ሚና | አፍሪቃ | DW | 08.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ ቀውስ እና የአልጀሪያ ሚና

የአፍሪቃ ህብረት፡ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ፡ በምህፃሩ ኤኮዋስ፡ የተመድ እና የአውሮጳ ህብረት የጦር ጠበብት እና የመከላከያ ሚንስትሮች፡ ባለፈው ሣምንት በማሊ መዲና ባማኮ ባካሄዱት ምክክር ላይ ሰሜናዊ ማሊን በተቆጣጠሩት አክራሪ ሙሥሊሞች አንፃር ወታደራዊ ርምጃ መውሰድ የሚቻልበትን የመፍትሔ ሀሳብ አፈላልገዋል።

የተለያዩ አፍሪቃውያት ሀገራትም ትናንት በዚያው በባማኮ ስለነዚህ ሀሳቦች ተወያይተዋል። የኤኮዋስ አባል ሀገራት ወደ ማሊ የጦር ርምጃ የሚወስዱ ወታደሮችንና የፀጥታ ኃይላትን ለመላክ ቀደም ሲል ተስማምተዋል። በዚሁ የባማኮ ምክክር ላይ የአልጀርያ ተወካዮችም ተካፋዮች ነበሩ። ይህችው ሰሜን አፍሪቃዊት ሀገር የማሊ ጎረቤት የኤኮዋስ አባል ባትሆንም፡ ለማሊው ቀውስ በማፈላለጉ ሂደት ላይ ግን ትልቅ ሚና ይዛለች።
አልጀሪያ ከማሊ ጋ፡ ማለትም በአክራሪ ሙሥሊሞች ከተያዘው ሰሜናዊ የሀገሪቱ ከፊል ጋ 1,300 ኪሎ ሜትር የጋራ ድንበር አላት። ይኸው ረጅሙ የጋራ ድንበር ራሱ አልጀሪያ በማሊ ውዝግብ ድርድር ላይ መያዝ ያለባትን ዋነኛ ቦታ ግልጽ አድርጓታል። ከዚህ ሌላ ደግሞ በሚገባ የታጠቀ ጦር ያላት አልጀሪያ በሀገርዋ በሚገኙ ፅንፈኞች አንፃር የትግል ተሞክሮ አካብታለች። ካለ አልጀሪያ ድጋፍ የማሊ ቀውስ መፍትሔ እንደማይገኝለት ጠበብት ተስማምተዋል። አልጀሪያ ተዕኮውን አልደገፈችውም። ይኸው አልጀሪያ በማሊ ይጀመር የሚባለውን የጦር ተልዕኮ የተቃወመችበት ድርጊት በወቅቱ ችግር ፈጥሮዋል።

በበርሊን የመገናኛ ዘዴ ጉዳይ አጥኚ ተቋም የፖለቲካ ተንታኝ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አዋቂ አሲየም ኧል ዲፍራዊ ግምት ግን፡ አልጀሪያ ተልዕኮውን ብትደግፍ ማሊን ብቻ ሳይሆን ራስዋንም ልትረዳ በቻለች ነበር።
የአፍሪቃ ህብረት፡ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት የኤኮኖሚ ማህበረሰብ፡ በምህፃሩ ኤኮዋስ፡ የተመድ እና የአውሮጷ ህብረት የጦር ጠበብት እና የመከላከያ ሚንስትሮች፡ ባለፈው ሣምንት በማሊ መዲና ባማኮ ባካሄዱት ምክክር ላይ ሰሜናዊ ማሊን በተቆጣጠሩት አክራሪ ሙሥሊሞች አንፃር ወታደራዊ ርምጃ መውሰድ የሚቻልበትን የመፍትሔ ሀሳብ ማፈላለጋቸው የሚታወስ ነው።

የተለያዩ አፍሪቃውያት ሀገራት ትናንት በዚያው በባማኮ ስለነዚህ ሀሳቦች ተወያይተዋል። የኤኮዋስ አባል ሀገራት ወደ ማሊ የጦር ርምጃ የሚወስዱ ወታደሮችና የፀጥታ ኃይላት ለመላክ ቀደም ሲል ስምምነታቸውን መስጠታቸው አይዘነጋም። በዚሁ የባማኮ ምክክር ላይ የአልጀርያ ተወካዮችም ተካፋዮች ነበሩ። ፍሪድሪከ ሚውለር እንደዘገበችው፡ ይህችው የማሊ ጎረቤት ሀገር የኤኮዋስ አባል ባትሆንም፡ ለማሊው ቀውስ በማፈላለጉ ሂደት ላይ ግን ትልቅ ሚና ይዛለች።
አልጀሪያ ከማሊ ጋ፡ ማለትም በአክራሪ ሙሥሊሞች ከተያዘው ሰሜናዊ የሀገሪቱ ከፊል ጋ 1,300 ኪሎ ሜትር የጋራ ድንበር አላት። ይኸው ረጅሙ የጋራ ድንበር ራሱ አልጀሪያን በድርድሩ ዋነኛ ቦታ እንድትይዝ አድርጓታል። ከዚህ ሌላ ደግሞ በሚገባ የታጠቀ ጦር ያላት አልጀሪያ በሀገርዋ በሚገኙ ፅንፈኞች አንፃር የትግል ተሞክሮ አካብታለች። ካለ አልጀሪያ ድጋፍ የማሊ ቀውስ መፍትሔ እንደማይገኝለት ጠበብት ተስማምተዋል። አልጀሪያ ተልዕኮውን አልደገፈችም። በማሊ ይጀመር የሚባለውን የጦር ተልዕኮ አልጀሪያ የተቃወመችበት ድርጊትም ችግር ፈጥሮዋል።

በበርሊን የመገናኛ ዘዴ ጉዳይ አጥኚ ተቋም የፖለቲካ ተንታኝ እና የመካከለኛው ምሥራቅ አዋቂ አሲየም ኧል ዲፍራዊ ግምት ግን፡ አልጀሪያ ተልዕኮውን ብትደግፍ ማሊን ልትረዳ በቻለች ነበር።
« ድጋፍ መስጠቱ በሁለት መንገድ ሊታይ ይችላል። ባንድ በኩል አልጀሪያውያን ምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል ገና ባልታወቀ የውጭ ውዝግብ ውስጥ ጣልቃ መግባት ያስፈራቸዋል። በሌላ ወገን ግን አልጀሪያ ተልዕኮውን ብትደግፍ ኖሮ አል ቓይዳ በእሥላማዊው ማግሬብ የመደምሰስ ዕጣ እንደሚገጥመው ለማሳየት በቻለች ነበር። »
ሰሜናዊ ማሊን እአአ ካለፈው ሚያዝያ፡ 2012 ዓም ወዲህ ከተቆጣጠሩት ቡድኖች መካከል አንዱ ከአል ቓይዳ ቅርበት አለው የሚባለው ሙዣዎ የተባለው ሲሆን፡ ሌላው አክራሪው የቱዋሬግ አንሳር ዲን ቡድን ነው። አልጀሪያ ካሁን ቀደም በማሊ የቱዋሬግ ዓመፅን በማርገቡ ረገድ ወሳኝ ሚና መጫወቷን የዓለም አቀፉ ውዝግብ ተመልካች ተቋም፡ ክራይስስ ግሩፕ ባልደረባ ዢል ያቢ ያስታውሳሉ።
« በወቅቱ በሚታየው የማሊ ቀውስ - በአልጀሪያ እና በአንሳር ዲን መካከል ግንኙነት አለ። ይኸው ቡድን የአልጀሪያ ባለሥልጣናት በሚገባ በሚያውቁት የቱዋሬግ ተወላጅ ያድ አጅ ጋሊ ይመራል። እንደሚታወሰው ፡ ቀደም ባለ ጊዜ በአልጀሪያውያን ሸምጋይነት በተደረሰ እና በአልጀሪያ በተፈረመ አንድ የሰላም ውል ላይ አልጀሪያ ትልቅ ሚና ነበራት። አልጀሪያ ይህንን የውል ሰነድ በሚገባ ጠንቅቃ ታውቃለች። ሆኖም፡ የፀጥታውን ሁኔታ በተመለከተ አሁን ያደረባትን ስጋት መረዳቱ አይከብድም። »

--- 2012_07_26_kampf_terror_sahel.psd

ከአል ቓይዳ ጋ ግንኙነት አላቸው የሚባሉ ቡድኖች የሚገኙባቸው ሀገራት


አልጀሪያ ተልዕኮውን የተቃወመችበት አንዱ ምክንያት የቀድሞ ቅኝ ገዢ ፈረንሣይ ወደ ማሊ የጦር ተልዕኮ እንዲላክ መገፋፋት የያዘችበት ድርጊት መሆኑን ኤል ዲፍራዊ ያስረዳሉ።
« አልጀሪያውያን በፈረንሣይ ቅኝ አገዛዝ አንፃር እጅግ አስከፊ ደም አፋሳሽ ጦርነት ማካሄዳቸውን እና እስከዛሬም በቀድሞዋ ቅኝ ገዢ ላይ ስር የሰደደ ጥላቻ እንዳላቸው ማስታወስ የግድ ነው። እና አሁን ከፈረንሣይ ጋ በአንድ የጦር ተልዕኮ ባንድነት መስራቱ ለአልጀሪያውያን እጅግ ከባድ ነው። »
በዚህም የተነሳ የማሊው የጦር ተልዕኮ በፈረንሣይ ፈንታ በዩኤስ አሜሪካ ገፋፊነት ቢቃቃ ኖሮ፡ አልጀሪያ ተልዕኮውን ልትደግፈው ትችል ነበር ተብሎ ይታሰባል። የዩኤስ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሂለሪ ክሊንተን ባለፈው ሣምንት ወደ አልጀሪያ በመሄድ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አብደልአዚዝ ቡቴፍሊካ የማሊውን የጦር ተልዕኮ እንዲደግፉ ለማግባባት ሞክረው ነበር።
ዶይቸ ቬለ የማሊን የጦር ተልዕኮ በተመለከተ የአልጀሪያ መንግሥትን አቋም ለማወቅ ያደረገው ሙከራው እስካሁን መልስ አላገኘም። አልጀሪያ ደገፈች አልደገፈች ግን ፡ የማሊ ተልዕኮ ካለዚችው ሀገር ተሳትፎ ማካሄዱ እንደማይቀር አያጠራጥርም። ወደማሊ የሚላከውን ዓለም አቀፉ የጦር ኃይልን የሚመለከተው ዕቅድ በዚህ በተያዘው የህዳር ወር ለተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት መቅረብ ይኖርበታል።

ፍሪድሪከ ሚውለር/አርያም ተክሌ

ተክሌ የኋላ

DW.COM

Audios and videos on the topic