የማሊ መፈንቅለ መንግሥት አንደኛ ዓመት | አፍሪቃ | DW | 21.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊ መፈንቅለ መንግሥት አንደኛ ዓመት

ሳኖጎ ተካፈሉም አልተካፈሉ፥ ፕሮፌሴር ትራኦሬ እንደሚያምኑት ማሊ ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ ቢያንስ የአንድ ዓመት ዝግጅት ያስፈልጋታል።ዘመናት ያስቆጠረዉ የቱአሬጎች የመብት ጥያቄም በፈረንሳዮች ጠመንጃ ተዳፈነ እንጂ መፍትሔ አላገኘም።እና ማሊ በርግጥ ሠላም ነች።

GettyImages 160772032 Children search on February 5, 2013 in the ruins of a hotel destroyed by French air strikes in Douentza.The town was retaken by French and Malian troops in January. AFP PHOTO / PASCAL GUYOT (Photo credit should read PASCAL GUYOT/AFP/Getty Images)

የጦርነቱ ገፅታ

የማሊ የጦር መኮንኖች የሐገሪቱን ፕሬዝዳት አማዱ ቱማኒ ቱሬን ከሥልጣ ካስወገዱ ዛሬ አንደኛ ዓመቱን ደፈነ።የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች፥ የአፍሪቃ ሕብረት፥ የምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ (ኤኮዋስ)ና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ባደረገባቸዉ ግፊት ሥልጣኑን ለሲቢል ቢያስረክቡም፥ የመፈንቅሉ መዘዝ ማሊን ሲያብጣት ነዉ የከረመዉ።በመፈንቅለ መንግሥቱ ሰበብ የተጠናከሩት ሙስሊም አማፂያና የቱአሬግ ደፈጣ ተዋጊዎች ሥጋት በፈረንሳይ ጦር ጥቃት ተገትቷል።በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሐገር አሁንም አስተማማኝ ሠላም መስፈኑና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረቱ እንዳጠያየቀ ነዉ።ፔተር ሒለ እና ያያ ኮንቴ የዘገቡትን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።ሻምበል አማዱ ሳኖጎ የመሯቸዉ የማሊ የመስመር መኮንኖች የዛሬ ዓመት የዛሬን ዕለት ያደረጉት፥ ፕሬዝዳት አማዱ ቱማኒ ቱሬን ከሥልጣን አስወግዶ፥ ቢያበቃ ኖሮ-እሰየዉ ባሰኘ ነበር።የማሊን ማዕከላዊ መንግሥት አናግቶ፥የሐገሪቱን ጦር ሽባ ማድረጉ-እንጂ የማሊ የእስካሁን አበሳ።

መፈንቅለ መንግሥቱ ሰሜናዊ ማሊ አድፍጠዉ ለነበሩት ለአክራሪ ሙስሊም እና ለቱአሬግ ደፈጣ ተዋጊዎች ያልደገሱት «ሠርግ» ብጤ ነበር-የሆነዉ።አማፂያኑ በመፈንቅለ መንግሥቱ የተሽመደመደዉን የማሊ መንግሥት ጦርን እየረመረሙ፥ የሰማናዊ ማሊ ከተሞችን ተራበራ ሲረከቡ ሕዝቡ ቤት፥ ንብረት መንደሩን ጥሎ ይሸሽ ያዘ።አብዛኛዉ ቁል ቁል ወደ ደቡብ ነዉ-የወረደዉ።ዋና መድረሻ ርዕሠ-ከተማ ባማኮ።

በመፈንቅለ መንግሥት የተጀመረዉ፥ በፈረንሳይ ጦር ድብደባና ድል የዓመት ጉዞዉን ሲያጠናቅቅ፥ ያ የሰሜን ማሊ መከረኛ ሕዝብ ሽቅብ ይወጣ ጀመር።ባማኮ አዉቶቡስ ተራ።

Mali's junta leader Amadou Haya Sanogo poses for a picture after agreeing to hand over power to the president of the National Assembly at his office at a military base in Kati in this April 7, 2012 file photo. When former colonial power France sent warplanes and troops to Mali on January 11, 2013 in a historic intervention, it did not just halt a menacing advance on the capital Bamako by Islamist rebels allied to al Qaeda. It also snuffed out what diplomats and local politicians say was a political conspiracy in the capital to oust Mali's interim civilian rulers, an attempted replay of the March 2012 coup that had plunged the Sahel state into turmoil and made it a potential launch pad for attacks on Western interests. To match Insight MALI-RECONSTRUCTION/ REUTERS/Joe Penney (MALI - Tags: POLITICS PROFILE CIVIL UNREST CONFLICT MILITARY)

የመፈቅለ መንግሥቱ መሪ ሻምበል ሳኖጎ«አዎ፥ ሁሉም እየተጣደፈ ነዉ።ሁሉም ወደ ቀየዉ መመለስ ይፈልጋል።» ይላሉ እሳቸዉ፥-እኝሕኛዉም አከሉ፥-

«በስተመጨረሻዉ ከዚሕ ልንለቅ ነዉ። እዚሕ ደቡብ ጥሩ ስሜት የለንም።ወደ መኖሪያችን መመለስ አለብን።አሁን ሠላም ነዉ።»

እያሉ።ባለፈዉ ጥር የአማፂያኑን ይዞታ መደብደብ የጀመረዉ የፈረንሳይ ጦር የሰሜን ማሊን ትላልቅ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።በእቅዱ መሠረት የኤኮዋስ አባል ሐገራትና የቻድ ወታደሮች የማሊን ሠላም ያስከብሯሉ።የጀርመንን ጨምሮ የአዉሮጳ ሕብረት አባል ሐገራት ወታደሮች ደግሞ የማሊን ጦር ያሠልጥናሉ።

ጀርመን እስካሁንም ለፈረንሳይና ለአፍሪቃ ወታደሮች የሥንቅ፥የትጥቅና የመጓጓዣ አገልግሎት ሰጥታለች።ለፈረንሳይ የጦር ጄቶች አየር በየአር ነዳጅ የሚሞላ አዉሮፕላንም አዝምታለች።የጀርመኑ የአየር ሐይል ባልደረባ ሌፍትናንት ኮሎኔል ዮርግ ባርትል እንደሚሉት ድጋፉ ላጠቃላይ ዘመቻዉ ጠቃሚ ነበር።

«የአዉሮፕላን ማጓጓዣዉም ሆነ የአየር በየአር ነዳጅ የመሙላቱ ተልዕኮ ብዙ ያልተለመደ ነዉ።ላጠቃላይ ዘመቻዉ ግን በጣም አስፈላጊ ነበር።»

የፈረንሳይ ጦር ዉጊያ፥ የአፍሪቃ ጦር ዘመቻ እና የጀርመኖችን አይነቱ ድጋፍ ሰሜናዊ ማሊን ቢያንስ ላሁኑ ከአማፂያን አፅድቷል።ዘላቂ ሠላም ሠፍኗል ለማለት ግን ጊዜዉ ገና ነዉ።ዲሞክራሲያዊ መንግሥትም ገና አልተመሠረተም።ባለፈዉ ሚያዚያ የፕሬዝዳትነቱን ሥልጣን ከጦር መኮንኖቹ የተረከቡት ዲዮንኩንዳ ትራኦሬ ለመጪዉ ሐምሌ አጠቃላይ ምርጫ ጠርተዋል።የፖለካ ተንታኝ ፕሮፌሰር ጀንባ ትራኦሬ እንደሚሉት ግን በዚሕ አጭር ጊዜ ፍትሐዊ ምርጫ ማዘጋጀት ከባድ ነዉ።

Titel: DW_ Tuareg_Burkina-Faso3: Schlagworte: Tuareg, Mali, Burkina Faso, Flüchtlinge, Befreiungsbewegung von Azawad Wer hat das Bild gemacht/Fotograf?: Katrin Gänsler Wann wurde das Bild gemacht?: 12. März 2013 Wo wurde das Bild aufgenommen?: Djibo, Burkina Faso

ቱአሬጎች

«ጥሩ ምርጫ ይሆናል? ተዓማኒነት ያለዉ ምርጫ ይሆናል? የሰሜኑ ሕዝብ በምርጫዉ እንዲካፈል ከፈለግን ምርጫዉን በጥንቃቄ ማዘጋጀት አለብን።እኔ ግን በዚሕ አጭር ጊዜ ዉስጥ ተአማኒነት ያለዉ ምርጫ ማዘጋጀት ይቻላል ብዬ አላምንም።»

የመንፈንቅለ መንግሥቱ መሪ ሻምበል ሳኖጎ በምርጫዉ እንደማይከፈሉ አስታዉቀዋል።ሳኖጎ ተካፈሉም አልተካፈሉ፥ ፕሮፌሴር ትራኦሬ እንደሚያምኑት ማሊ ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ ቢያንስ የአንድ ዓመት ዝግጅት ያስፈልጋታል።ዘመናት ያስቆጠረዉ የቱአሬጎች የመብት ጥያቄም በፈረንሳዮች ጠመንጃ ተዳፈነ እንጂ መፍትሔ አላገኘም።እና ማሊ በርግጥ ሠላም ነች።

ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ


Audios and videos on the topic