የማሊው ምርጫ፣ | አፍሪቃ | DW | 29.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የማሊው ምርጫ፣

በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር በማሊ፣ እንደተፈራው ሳይሆን የትናንቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሰላም ነው የተከናወነው። የዶቸ ቬለ ባልደረባ ፣ ካትሪን ጌንትስለር፣ ከማሊ የላከችው ዘገባ እንደሚጠቁመው፣ከ 27 ቱ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል፤

ኢብራሂም ቡባካር ኬይታ የተባሉት፣ የምርጫው አሸናፊ ሳይሆኑ አይቀሩም። ምርጫዉን ለመታዘብ እዚያ የሚገኘዉ የኅብረቱ ታዛቢ ቡድን መሪ ሉዊ ሚሼል ምርጫዉ ግልፅነት የታየበትና በጥሩ ሁኔታ መካሄዱንም ገልጸዋል። ምርጫዉ ሰላማዊና በርካታ ህዝብ የተሳተፈበት እንደነበር በማመልከትም መራጩ ህዝብ ድምጹ ምን እንደሚያመጣ በግልጽ የተረዳ ነበርም ብለዋል። ካትሪን የላከችውን ዘገባ፣ የበርሊኑ ዘጋቢአችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic