የሙዝ አግልግሎት፣ በኃይል ምንጭነት፣ | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 10.06.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የሙዝ አግልግሎት፣ በኃይል ምንጭነት፣

ምንጩ በላቲን አሜሪካ ሆኖ፣ ከዚያ ወደ ሌሎች አገሮች የተስፋፋው፣ እጅግ ታዋቂና ጣፋጭ ፍሬ፣ ሙዝ ነው! ይኸው ተወዳጅ ፍሬ፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በ 107 አገሮች የሚመረት ሲሆን፣

default

በያመቱ ፣ የሚሰበሰበው ፣ መጠኑ፣ በአጠቃላይ 92 ሚሊዮን ቶን ገደማ ነው። ሙዝ፣ ፍሬው ከተበላ በኋላ ፣ ልጣጩ በቆሻሻነት እንደሚጣል የታወቀ ነው። ይሁንና ፣ ለማገዶ ሲባል፣ አጸድ እየተቆረጠ፣ ቁጥቋጦ እየተመነጠረ ፣ በተፈጥሮ አካባቢ ላይ ብርቱ ጉዳት እየደረሰ ባለበት ባሁኑ ዘመን፣ በያይነቱ፣ አማራጭ ማገዶችን መሻቱ ብልህነት ነው። መላውንም ሆነ ብልሃቱን ደግሞ በዘመናዊው ሥነ-ቴክኒክ በመታገዝ ፣ውጤት እንዲያሳይ ማድረግ የሚያዳግት አለመሆኑን ፣በእንግሊዝ ሀገር ፣ በ Nottingham ዩኒቨርስቲ የተደረገው ሙከራ ያስረዳል። በኢንዱስትሪ በበለጸጉት አገሮች፣ በተፈጥሮ ጋዝ፣ ወይም በኤልክትሪክ ኃይል ምግብ ማብሰል በየቤቱ የተለመደ ነው። በአዳጊ አገሮች ፣ ብዙ ሰዎች እንዲህ የተመቻቸ የምግብ ማብሰያው የኃይል ምንጭ እንዲህ አልተመቻቸላቸውም። በነቲንግሃም ዩኒቨርስቲ፣ የ ኢንጂኔሪንግ ፕሮፌሰር ፣ ማይክ ክሊፈርድ እንዲህ ይላሉ።

«የግማሹ ዓለም ህዝብ፣ ምግብ የሚያበስለው በእንጨት፣ በግንድም ሆነ ፍልጥ ነው። በዚህ የሚጠቀመው ህዝብ 3 ቢሊዮን ገደማ ይሆናል። ስለዚህ ዐቢይ ችግር በመሆኑ የሚቃጠለውን የአንጨት መጠን ለመቀነስ ሳይንስን በአግባቡ መጠቀም ይቻላል። ህዝቡ ለማገዶ ፣ ለምግብ ማብሰያ የሚጨፈጨፈውን ደን፣ የሚባክነውን እንጨት፣ መግታት የምንችለው፣ በዘዴ ስንጠቀም ነው። በዓለም ዙሪያ የምድር ግለት እንዲጨምር ያደረገውን የተቃጠላ አየር ም መቀነስ እንችላለን። »

በበርሚንግሃም ዩኒቨርስቲ፣ የኢንጅኔሪንግ ፣ የከፍተኛ ትምህርት መምህራን ከሆኑት፣ የ ፕሮፌሰር ማይክ ክሊፈርድ ባልደረቦች መካከል የማሺን ኢንጅኔር Joel Chaney በበኩላቸው ሲያብራሩ---

«በዓለም ዙሪያ በያመቱ 92 ሚልዮን ቶን ሙዝ ይመረታል። ሙዙ የሚበቅልውም ሆነ የሚመረተው በ 107 አገሮች፣ በ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ነው። »

ክሊፎርድ፣ ቸኒና ባልደረቦቻቸው እንደሚሉት ከሙዝ አንዳች የሚጣል ጥቅም- የለሽ የሚባል ክፍል የለም። ፍሬው ብቻ 10 ከመቶ ድርሻ ሲኖረው የተቀረው ዋናው ግንድ፣ ቅርንጫፉና ቅጠሉ ጥቅም እንደሌለው ቆሻሻ የሚጣል ነበረ። እንግሊዛውያኑ ተማራማሪዎች ግን፣ ከሙዝ አንዳች የሚጣል ነገር እንደማይኖር እያሳዩ ነው። እምብዛም አድካሚ ባልሆን ሥነ- ቴክኒክ፣ ከሚቆረጥ የሙዝ ግንድ፣ ቅርንጫፍና ቅጠል እንዲሁም የፍሬ ልጣጭ፣ በማሺን ግፊት ኃይል፣ ልክ እንደኩበትም ሆነ የእበት ጥፍጥፍ ለማገዶ የሚሆን በጡብ ቅርጽ የሚሠራ የኅይል ምንጭ ለማቅረብ ችለዋል። ይህ እንግዲህ ቸኒ እንደሚሉት ለማገዶ እንጨትን የሚተካ ነው።

«በኢንዱስትሪ ኩባንያዎች፣ ከፍተኛ ግፊትን በመጠቀም ከሙዝ ልጣጭ፣ ቅጠልና ግንድ የሚነድ ጡብ ያመርታሉ። የሙዝ ልጣጭ ጡብ እንግዲህ እንዲህ ነው የሚሠራው። በዚህ ዓይነት ፣ በየመንደሩ ፣ ማንኛውም ሰው፣ በቀላሉ በእጁም ቢሆን በመጠፍጠፍ መሥራት ይችላል። ምክንያቱም ሁሉም አንድ ላይ ተጠራቅሞ ሲበሰብስ ፣ በቀላሉ ጡብ እያስመሰሉ ለመጠፍጠፍ የሚያስቸግር አይሆንም። በአንድ ቀን ውስጥ በዛ ያለ ለማገዶ የሚውል ለብዙ ቤተሰብ የሚያገልግል፤ የሙዝ ልጣጭ ጡብ መሥራት ይቻላል። »

ተክሌ የኋላ/ሸዋዬ ለገሠ