የሙዚቃ ድግስ የከባቢ አየር ሙቀትን ለመቀነስ | ባህል | DW | 08.07.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የሙዚቃ ድግስ የከባቢ አየር ሙቀትን ለመቀነስ

ባለፈዉ ሳምንታት ዉስጥ ጅቡቲ ዉስጥ 30 ጥንዶች ትዳር መሰረቱ አሉ። 30 ጥንድ ምነዉ በአድዜ ግዜ ቢባል ጅቡቲ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የተላቀቀችበትን ብሄራዊ የአል ቀን ምክንያት በማድረግ ነበር ነዉ። የሚገርመዉ 30 ጥንድም የተመረጠዉ ጅቡቲ ልክ የዛሪ 30 አመት ከፈረንሳይ ቅኝ ነጻ የወጣች ሰለነበር ነዉ። ታድያ የዛሪ ሰላሳ አመት ጅቡቲ ከፈረንሳይ ስትላቀቅ ለፈረንሳይ ጅቡቲ የመጨረሻዋ በቅኝ ግዛት የያዘቻት አገርም ነበረች። በሌላ በኩል ትናንትና የአዉሮፓዉያኑን የ

LIVE EARTH በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ

LIVE EARTH በደቡብ አፍሪቃ ጆሃንስበርግ

ቀን ቀመር ለሚከተሉ ለየት ያለ ቀን ነበር።

ወር ከገባ 7ኛ ቀን 7ኛ ወር እናም 2007 አ.ም ልብ በሉ 7ኛ ቀን 7ኛ ወር 2007 አ.ም። ሰባት ሰባት የገጠመበት ለየት ያለ ቀን በማለት ያምኑበታል ተመሳሳይ ቁጥር በአንድ ቀን ሲገጥም። ታድያ ይህን አስታከዉ በእለቱ ትዳራቸዉን የመሰረቱ ፣ መሃላ የተገባቡ ጥንዶች በርካታ ነበሩ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ዋላችሁ ይህንን ያነሳሁላችሁን ጉዳይ ወደ ኳላ ላይ እመለስበታለሁ በመጀመርያ ግን በትናንትናዉ እለት በሰባቱም አህጉራት የከባቢ አየር ሙቀት መጨመር መንስኤ የሆኑትን ችግሮች ማስወገድ አለብን በሚል፣ ታዋቂ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች ታላቅ የሙዚቃ ድግሳቸዉን በስምንት የተለያዩ አገሮች አሳይተዋል። LIVE EARTH የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ይኸዉ የሙዚቃ ትርኢት በአለም ዙርያ በሚገኙ ከ100 በላይ አገሮች በራድዮና በቴሌቭዥን አማካኝነት በቀጥታ ስርጭት ተላልፎአል። ይህን የሙዚቃ ድግስ በአለም ዙርያ ከሁለት ቢሊዮን ህዝብ በላይ ተከታትሎታል የሚል ግምትም አለ። የዛሪዉ የባህል መድረከቻን ትናንት በአለም ዙርያ ስለተስተጋባዉ የሙዚቃ ትርኢት እና ተልዕኮዉ፣ በተጨማሪ በጅምላ ስለተካሄደዉ ሰርግ በጥቂቱ ሊያወጋችሁ ተሰናድቶአል አብራችሁን ቆዩ።