የሙዚቃ አቀነባባሪና የሒሳብ አያያዝ ባለሙያ | ባህል | DW | 16.01.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የሙዚቃ አቀነባባሪና የሒሳብ አያያዝ ባለሙያ

በውነህ ስለሺ ለኪነ ጥበብ ልዩ ፍቅር አለው፤ የተሰማራው ግን በቀለም ሙያ ነው። ለምን? ይገልፅልናል።

Klaviatur

በውነህ ስለሺ ያደገው እና ትምህርቱን የተከታተለው ድሬደዋ ከተማ ነው። የተለያዩ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ይጫወታል፤ ሙዚቃ ያቀናብራል እንዲሁም የሒሳብ አያያዝ ሰራተኛ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ የተለማመደው የሙዚቃ መሣሪያ ክራር ነው።በውነህ የሙዚቃ ችሎታ ብቻ አይደለም ያለው፤ በትምህርቱም ጎበዝ እንደነበር ገልፆልናል።

እሱም ይሁን ቤተሰቡ ለሙዚቃ መሣሪያ ልዩ ፍቅር ቢኖራቸውም፤ ወላጆቹ ግን ልጃቸው ወደ ቀለሙ ትምህርት እንዲያደላ ነው በመጀመሪያ የገፋፉት። ስለሆነም የሒሳብ አያያዝ ሙያ ለመማር ወደ ባህርዳር ዩንቨርስቲ አምርቶ ፤ የመጀመሪያ ዲግሪውን ግዟል።ዩንቨርስቲ ገብቶ መማሩ፤ ዛሬ ላይ ጠቅሞታል፤ መተዳደሪውም ነው። «ነገር ግን ተገድጄ ነው ይላል» የተገደደው ከገንዘብ ማግኛ አንፃር ነው። ወጣቱ የሙዚቃው ትምህርት ቤት ገብቶ ቢሆን ኖሮ እውቀቱን ይበልጥ ማዳበር እንደሚችል ርግጠኛ ነው።

በውነህ የሚጫወታቸው መሣሪያዎችን በመጠኑ ተጫውቶልናል። ከበውነህ ጋር የነበረንን ቆይታ በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic