የሙንሽኑ ገንዘብ አሳታሚ ድርጅት እና ከሙጋቤ ጋር ያለዉ ልዩ ወዳጅነት | አፍሪቃ | DW | 28.03.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሙንሽኑ ገንዘብ አሳታሚ ድርጅት እና ከሙጋቤ ጋር ያለዉ ልዩ ወዳጅነት

በመጭዉ የሳምንት መጠናቀቅያ ላይ ዝንባቤዌ የፕሪዝደንት ምርጫ ታካሂዳለች። ለሙጋቤም የቀድሞዉ የአገሪትዋ የገንዘብ ሚኒስቴር Simba Makoni ታላቅ ተፎካካሪ ሆነዉባቸዋል።

ሙጋቤ ለአገሪትዋ ወታደሮች እንዲሁም ለገዢዉ መደብ ታማኝ ለሆኑ አስተማሪዎች የደምወዝ ጭማሪ አድርገዋል

ሙጋቤ ለአገሪትዋ ወታደሮች እንዲሁም ለገዢዉ መደብ ታማኝ ለሆኑ አስተማሪዎች የደምወዝ ጭማሪ አድርገዋል

ቀድሞ በኢኮኖሚ እድገትዋ በአፍሪቃ ተጠቃሽ የነበረችዉ ዝንባቤ፣ ዛሪ ሊነገር በሚያዳግተዉ የገንዘብ ግሽፈት ዉስጥ በመዘፈቅዋ፣ ለምርጫዉ መሰናዶ ደጋፊዎችን ለመመስብ እንዲያስችል ገንዘብ ማሳተሟን ቀጥላለች። ታድያ ይህ አምባ ገነን መንግስት በገንዘብ ህትመት ለአመታት በመርዳት ላይ ያለዉ በጀርመን በሙንሽን ከተማ የሚገኘዉ ማተምያ ቤት መሆኑ ነገሩን አስገራሚ አድርጎታል። Giesecke & Devrient የተሰኘዉ የሙንሽኑ ማተምያ ቤት እና የዝንባቤ መንግስት ወዳጅነት የጀመሩት በ 70 ዎቹ አመታት በዝንባቤ የነበረዉ የ ስሚዝ መንግስት ከወደቀ ወድያ መሆኑ ታዉቆአል። የዶቸ-ቬለዉ ሉድገር ሻዶምስኪ ዝርዝር ዘገባዉን አጠናቅሮታል። አዜብ ታደሰ እንዲህ ታቀርበዋለች።