የሙስሊሞች ተቃዉሞና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 26.07.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሙስሊሞች ተቃዉሞና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ

ወራት ያስቆጠረዉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ምዕመናን አቤቱታና ሰላማዊ ተቃዉሞ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደረጃዉ ከፍ እያለ መሄዱ እየተዘገበ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት ማለቂያ ቅዳሜ የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች መንግስት በሃይማኖታችን ጣይቃ ገብቷል ካሉ ሙስሊም

 አማንያን ጋ መጋጨቱ ሮይተርስ ዘግቧል።  በተፈጠረዉ መፋጠጥም ቤተዕምነታቸዉ ዉስጥ የፀጥታ ኃይሎች ገብተዉ አንዳንዶችን ሲያስሩ፤ በትር የደረሰባቸዉ እንዳሉም ተነግሯል። ዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች HRW ሁኔታዉን በጥሞታ እየተከታተለ እንደሚገን በመግለፅ፤ ለተባባሰዉ ሁኔታ መንስኤዉ የሀገሪቱ ህገ መንግስት አለመከበር እንደሆነ አመልክቷል። የድርጅቱን የአፍሪቃ ተመራማሪ ያነጋገረችዉ ሸዋዬ ለገሠ ዘገባ አጠናቅራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic