የሙሥሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሙሥሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ

ችሎቱ በተከሳሽ በእነ አቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ቃልም ማድመጥ ጀምሯል ። ዛሬ የአንዱን ተከሳሽ ቃል ያደመጠው ችሎቱ የተቀሩትን 18 ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ለማዳመጥ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል ።


ቃሊቲ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት በሙስሊም መሪዎች ተከሳሾች ጠበቆች የቀረበውንንና አቃቤ ህግ መቃወሚያ ያቀረበበትየመከላከያ ምስክሮች ጭብጥ ላይ ብይን ሰጠ ። ችሎቱ በተከሳሽ በእነ አቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ቃልም ማድመጥ ጀምሯል ። ዛሬ የአንዱን ተከሳሽ ቃል ያደመጠው ችሎቱ የተቀሩትን 18 ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ለማዳመጥ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic