የመጸዳጃ ስፍራ እጦት ከት/ት ገበታ ሲያስቀር | ወጣቶች | DW | 04.08.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ወጣቶች

የመጸዳጃ ስፍራ እጦት ከት/ት ገበታ ሲያስቀር

በኢትዮጵያ በተለይ በገጠራማው አካባቢ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የአካባቢ ጽዳት ጉድለት እና የግል ንፅህና ችግር ይስተዋላል። ይህ ችግር በርካታ ልጃገረዶች ጭራሽ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ ያደረገበት አጋጣሚ እንዳለ የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ገልጾልናል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 09:42

በንቲ ኤጄታ

በንቲ ኤጄታ የፊንላንድ እና የኢትዮጵያ መንግሥት በትብብር የሚሰሩበት COWASH በተባለ ድርጅት ባልደረባ ነዉ።

Benti Ejeta, COWASH, Äthiopien

በንቲ ኤጄታ

ድርጅቱ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ዋናዉ  የንፁህ ውኃ አቅርቦት ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና አገልግሎት ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 76 ወረዳዎች  ይሰራል።

በንቲ በዚህ መርኃ ግብር ስር  ሲሰራ አምስት አመት ተቆጥረዋል። ወደዚህ ስራ ከመግባቱ በፊት በጋዜጠኝነት ሙያ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ተብሎ ይጠራ በነበረው በንቲ ኢትዮጵያን እየተዘዋወረ ስላለው ችግር በታዘበበት እና በዘገበበት ወቅት የደረሰበት ድምዳሜ ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት ነው። በተለይ  ወጣት ሴት ተማሪዎች  የወር አበባ ሲታያቸው በውሃ እና በመፀዳጃ ቦታ ማጣት ምክንያት ተማሪዎች በወር ለአራት ቀን በትንሹ ከትምህርት ቤት እንደሚቀሩ እና ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንደማይችሉ በንቲ ይናገራል። ስለሆነም ሴቶች የመርኃ ግብሩ  ዋና ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያስረዳል።

በንቲ COWASH  በሚሰራባቸው ሀገራት በሙሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት ባካሄደው አንድ ውድድር ላይ ተሳትፎ «የ ቶን ሻውትን» ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። በተለይ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ የንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ ሰዎች ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ላይ ከዚህ የበለጠ መሰራት አለበት የሚለው በንቲ ኤጄታ ስለሽልማቱ እና ስለ ስራው ገልጾልናል።

ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።

 ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic