የመጋቢት 23 ቀን 2011 ስፖርት | ስፖርት | DW | 01.04.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

የመጋቢት 23 ቀን 2011 ስፖርት

በ43ኛው የዓለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የበላይ ሆና አጠናቃለች።  በዕለቱ የስፖርት መሰናዶ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን ውጤትና እንመለከታለን። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የወቅቱ ፕሬዝደንት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ ውድድሩን አስመልክቶ ላነሳንላት ጥያቄዎች አስተያየቷን ሰጥታናለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 08:37

የመጋቢት 23 ቀን 2011 ስፖርት

 በጎርጎሪዮሳዊው 2020ዓ,ም ጀምሮ የ10 ሺህ እና የ5 ሺህ ርቀት የሩጫ ውድድሮች ከዳይመንድ ሊግ ውድድር ውጪ እንዲሆኑ በቅርቡ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሕበር ምክር ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች አስተያየትም ተካቷል።  እግር ኳስንም ይቃኛል። ከዚህም ሌላ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው  ሐሙስ መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም የመግባቢያ ሰነድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ተፈራርሟል። የመግባቢያ ሰነዱ በ16 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዮች ጋር ሲፈራረም በሁለቱም ጾታ የአዳጊ ወጣቶች ስልጠና እንደሚሰጥ አቶ መኮንን ኩሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር ነግረውናል።  

ሃይማኖት ጥሩነት/ነጃት ኢብራሂም

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic