ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰነድ አጠባበቅ መግለጫችን ማግኘት ይችላሉ።
የጀርመን የሐገር ዉስጥ ጉዳይ ሚንስቴር አዲስ የተሻሻለዉን የዜግነትና የመኖሪያ ፈቃድ ረቂቅ ሕግን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ጀርመን እያረጀ የመጣዉን የሰራተኛ ኃይሏን ለመተካትና ባለሙያዎችን ለማማለል ከዚሕ ቀደም የነበረዉን የዜግነትና የመኖሪያ ፍቃድ ሕጓን አሻሽላለች።
በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ እስካሁን ቢያንስ ሰባት መስጊዶች በመንግስት ፈርሶብኛል ሲል አማረረ፡፡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በቅርቡ በአዲስ መልክ በተዋቀረው በሸገር ከተማ ፈርሷል ያለውን መስጊዶች በማስመልከት ለአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በደብዳቤ ማመልከቱንም አሳውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ሕገመንግሥቱን አስመልክቶ ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገውን ጥናት 16 የፖለቲካ ድርጅቶችን የተካተቱበት የተቃዋሚ ፖለቲካ ስብስብ አጣጥሎ ነቅፎታል ። ሕገመንግሥቱ አይነካብን የሚሉ እንዳሉ ሁሉ እንደውም ሙሉ በሙሉ ተቀዶ መጣል አለበት የሚሉም አሉ ። ከሁለቱም በተለየ መሻሻል አለበት የሚሉም ይታያሉ ።