1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች እና ተሞክሮዋቸው

ዓርብ፣ ግንቦት 21 2007

በአለፈው እሁድ በኢትዮጵያው 5ኛ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ የተካፈሉ በርካታ ወጣቶች ፤ ተሞክሮዋቸውን ሊያካፍሉን ፍቃደኛ ነበሩ። ከነዚህ ውስጥ ጥቂቱን ለማነጋገር ችላለች።

https://p.dw.com/p/1FXuN
Wahltag in Äthiopien Hosaena
ምስል DW/Y.-G. Egziabhare

የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች እና ተሞክሮዋቸው

አንድ መራጭ ለራሱ እና ለሀገሩ በጎ ሚና ይኖረዋል የሚለውን ፓርቲ እና የምርጫ እጩዎች አመዛዝኖ ከመወሰን በተጨማሪ፤ በምርጫው ሲሳተፍ የመጀመሪያ ጊዜው ከሆነ ብዙ ጥያቄዎችም ሊኖሩት ይችላሉ። የትኛው የምርጫ ጣቢያ ነው የምሄደው? እዛስ ስሄድ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ያለው የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል? መብት እና ግዴታዎቼ የትኞቹ ናቸው? እና ሌላም ሌላም ጥያቄዎች ። ለዛሬ ያነጋገርናቸው ወጣቶች በመላው ኢትዮጵያ እሁድ ዕለት በተካሄደው ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ የመረጡ ናቸው። በምርጫ ጣቢያ የነበረውን የምርጫ ሂደት እና ተሞክሮዋቸውን አካፍለውናል።

የ22 ዓመቱ የአዲስ አበባ ወጣት ፤ ፍሰሀ እሁድ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ተሳትፏል። ፍሰሃ፤ በምርጫ ጣቢያው ሲያስመርጡ የነበሩት ሰዎች የማውቃቸው የሰፈር ሰዎች ስለነበሩ፤ምንም ግራ አልተጋባውም ይላል።

Wahltag in Äthiopien
ምስል DW/T. Haile-Giorgis

ሌላው ወጣት የ 26 ዓመቱ ቻሌ ነው ከባህር ዳር። ምንም እንኳን ለ5 ዓመት በፊት በምርጫ የመሳተፍ እድል ቢኖረውም ሲመርጥ ዘንድሮ የመጀመሪያው ነው። በመቀሌ ከተማ የመረጠው የ 18 ዓመት ወጣት መሀመድ ደግሞ አስቀድሞ ስለምርጫ ሂደት የተገነዘበው እና በተግባር የገጠመው የተለያዩ እንደነበር ገልፆልናል።ሌላው ወጣት ከአዲስ አበባ የ 23 ዓመቱ ተመስገን ነው።

ምርጫውን እንደጠበኩት አግኝተዋለሁ ያለን ፍቃደ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ጊዜ የመምረጥ መብት ቢያገኝም እድሉን አልተጠቀመበትም። አሁን ግን የመረጥኩት የፖለቲካ ግንዛቤ በማግኘቴ ነው ይላል የ 28 ዓመቱ ወጣት።ሌላው ስለ መጀመሪያ የምርጫ ተሞክሮው ያካፈለን፤ ከወላይታ ሶዶ ፤ የ 18 ዓመቱ ታምራት ነው።ታምራት ወደ ምርጫ ጣቢያው የሄደው ከእናቱ ጋር ነበር።

በአለማያ ከተማ የ 22 ዓመት የተመስገን የፈለገውን ፓርቲ ቢመርጥም ለምርጫ ስለቀረቡት የክልሉ ተመራጭ እጩዎች አያውቅም ነበር።

የጥቂት ወጣት የመጀመሪያ ጊዜ መራጮች ተሞክሮን እና በኢትዮጵያ እየተዘዋወረ የዘገበው እሸቴ በቀለን አስተያየት ከዚህ በታች በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ