«የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስይዝ 19 ዓመቴ ነበር» ሲሳይ ሌሊሳ | ባህል | DW | 08.04.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

«የመጀመሪያ ዲግሪዬን ስይዝ 19 ዓመቴ ነበር» ሲሳይ ሌሊሳ

አንድ ሰው ነፃ የትምህርት እድል አግኝቶ እንዲማር ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ እንዳለበት ግልፅ ነው።የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ከነዚህ ተማሪዎች አንዱ ነው።

ሲሳይ ሌሊሳ ይባላል። በአሁኑ ሰዓት ተወልዶ ካደገባት አዲስ አበባ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ለመከታተል ጀርመን ለትምህርት ከመጣ 8 ወር አለፈው። ሲሳይ ዛሬ በጀርመን ሀገር ትምህርቱን መከታተል እንዲችል ከልጅነቱ ጀምሮ ለትምህርት ያለው ፍላጎት ረድቶታል። 6 ዓመት የሚፈጀውን ትምህርት በ3 ዓመት እንዳጠናቀቀ ነግሮናል።ስለሆነም የ4ኛ ክፍል ተማሪ ከነበረው ታላቅ ወንድሙ እኩል አብሮ አንድ ክፍል ለመማር ችሏል። ለዚህም አባቱ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። «አብዛኛውን ነገር እቤት አስተምሮኝ ስለነበር ትምህርት ቤት ስሄድ የሚያስተምሩት የማውቀውን ነገር ነበር » ይላል ሲሳይ። ወጣቱ ከመቀሌ ዮንቨርስቲ በተፈጥሮ ሀብት ምጣኔና አጠቃቀም የመጀመሪያ ዲግሪውን ሲያገኝ ገና 19 ዓመቱ ነበር።እሱ እንደሚለው ከክፍል ባልደረቦቹ ጋር ያለው የእድሜ ልዩነት ብዙም እረብሾት አያውቅም። ከዚህም ሌላ እንዴት ነፃ የትምህርት ዕድል እንዳገኘ አጫውቶናል።

ሙሉውን ዝግጅት ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic