የመድረክ መግለጫ | ኢትዮጵያ | DW | 01.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የመድረክ መግለጫ

መድረክ በጋዜጣዊ መግለጫው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ወደ ድርድር መድረክ እንዲመጣ ህዝቡና ዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብ ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ አሰተላልፏል

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:42

የመድረክ መግለጫየኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በአጭሩ መድረክ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ። በዚሁ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መንግሥት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የሚያሰሙትን ማሰሩና ማሰቃየቱ አለመቆሙ ተገልጿል ። ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከኦሮምያ ክልል በርካቶች ከህግ ውጭ በጥርጣሬ ተይዘው እንደታሰሩ ና እየተሰቃዩ እንደሆነም መድረክ መረጃ እንደደረሰው የፓርቲው ዋና ፀሃፊ በጋዜጣዊ መግለጫው ተናግረዋል ። መድረክ በጋዜጣዊ መግለጫው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግ ወደ ድርድር መድረክ እንዲመጣ ህዝቡና ዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብ ጫና እንዲያደርጉ ጥሪ አሰተላልፏል ።ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic