የመዋዕለ ህፃናት እጥረት በጀርመን | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.08.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የመዋዕለ ህፃናት እጥረት በጀርመን

የጀርመን መንግሥት እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ያለው የህፃናት ቁጥር እንዲጨመር እናቶች እንዲወልዱ የሚያበረታቱ ልዩ ልዩ ድጋፍና ድጎማዎችን ይሰጣል ።

default

ይሁንና አሁንም ጀርመን ውስጥ የሚወለዱ ህፃናት ቁጥር ከመጨመር ይልቅ እየቀነሰ መሆኑን የፌደራል ጀርመን ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ያወጣው አንድ ዘገባ ያመለክታል ። በዚሁ ዘገባ መሠረት ባለፈው የጎሮጎሮሳውያኑ 2010 ዓ.ም እድሜያቸው ከ 18 ዓመት በታች የሆነ ህፃናት ቁጥር ከዛሬ 10 ዓመቱ አሃዝ ጋር ሲነፃፀር በ 14 በመቶ ያነሰ ነው ። ለዚህም የልጆች መዋያ ቦታዎች እጥረት አንድ ምክንያት ሆኖ ይቀርባል ። የዶቼቬለዋ Daphne Grathwohl እንደዘገበችው በአሁኑ ሰዓት ጀርመን ውስጥ ከ 3 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት መዋያ ፈልጎ ማግኝት የስራ ፍለጋ ያህል ከብዷል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ

Audios and videos on the topic